#Fastmereja:-በደራሲ ወድነህ ክፍሌ ተደርሶ በአለምፀሐይ እጅጉ አዘጋጅነት የተዘጋጀው «የደመና ዳንከረኞች» የተሰኘው ተወዳጅ ቴአትር ከዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በይፋ መታየት መጀመሩ ተበሰረ።
ቴአትሩ የሰውን ደግነት፣ ስግብግብነት፣ ራስ ወዳድነት፣ ፍቅር፣ የእናት ለልጅ ያላትን ፍቅር እንዲሁም ልጅ የማጣትና የማሳደግ ውጣ ውረዶችን አጣጥፎ የያዘ ድቅቅ ያለ ማህበራዊ ጭብጥ ያለው ሥራ ነው።
ቀደም ሲል በታችኛው አዲሱ ቴአትር ቤት (ፍላሚንጎ) ይታይ የነበረ ቢሆንም፣ ከዛሬ ጀምሮ ወደ እናት ቤቱ ሀገር ፍቅርቴአትር በመመለስ ዘወትር ሐሙስ በ11፡30 ለተመልካች እንደሚቀርብ ነዉ የተገለፀዉ።
የቴአትር ክፍሉ እንዳስታወቀው የመግቢያ ትኬት ዋጋው 200 ብር ሲሆን፣ ተመልካቾች ትኬታቸውን በዘመናዊ የዲጂታል (ኦንላይን) ክፍያ ሥርዓት መቁረጥ እንደሚችሉም ተገልጿል።
የቴአትሩ አዘጋጅ አለምፀሐይ እጅጉ “ቴአትር ማየት ለአእምሮ ምግብ ነው” በማለት፣ የኪነ-ጥበብ አፍቃሪዎችና ተመልካቾች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በቦታው በመገኘት የተለፋበትን ይህንን ሥራ እንዲመለከቱና እንዲዝናኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።



Source: FastMereja









No comments yet.