#Ethiopia | የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን አርቲስቶች ከተቀላቀሉት በኋላ በፋይናንስ ረገድ የጎላ መሻሻል እያሳየ መሆኑ ተገለጸ
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን 20ኛውን የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር በታላቅ ዝግጅት ለማካሄድ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ፌደሬሽኑ ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የሚዘልቅ የ45 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ከቫርዳስ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።
በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እና በስምምነቱ ወቅት እንደተገለጸው ውድድሩ ከመስከረም 9 እስከ 26 ባሉት ቀናት ውስጥ በስድስት የከተማዋ እና በሁለት ተጋባዥ ክለቦች መካከል የሚካሄድ ይሆናል።
ስለ አዲስ አበባ ክለቦች የውጤትና የገንዘብ ችግር ማብራሪያ የሰጡት የፌደሬሽኑ አቃቤ ነዋይ አሰፋሽ ታገሰ ክለቦች ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወዲህ በሌሎች ክልሎችና ከተሞች ሲወዳደሩ በመቆየታቸው ለከፍተኛ የሆቴል፣ የትራንስፖርትና የሜዳ ኪራይ ወጪ ይዳረጉ እንደነበር አስታውሰዋል።
ዘንድሮ ውድድሮች በከተማዋ መካሄድ መጀመራቸው ይህንን የፋይናንስ ጫና ከመቀነሱም በላይ የስፖርቱ አፍቃሪ የሚወዳቸውን ቡድኖች በቅርበት እንዲከታተል ዕድል ይሰጣል።
በዘንድሮው የከተማ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ መቻል፣ ኢትዮጵያ መድን እና አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ ተጋባዦቹ አዳማ ከተማ እና ጋሞ ጨንቻ በድምሩ ስምንት ቡድኖች ይሳተፋሉ።
ከቫርዳስ ኩባንያ ጋር በተደረገው ውል መሠረት ፌደሬሽኑ በየዓመቱ 15 ሚሊዮን ብር የሚያገኝ ሲሆን ከተመልካች ትኬት ሽያጭ የሚሰበሰበው ገቢም ቀጥታ ለፌደሬሽኑ ገቢ የሚሆን ይሆናል።
በተጨማሪም ታዋቂ አርቲስቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በፌደሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚነት መካተታቸው የተቋሙን መልካም ገጽታ በመገንባትና ትልልቅ የኮርፖሬት ስፖንሰርሺፖችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጻል።
📸 ከበደ መክብብ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#AddisAbabaCityCup #AddisAbabaFootballFederation #EthiopianFootball #Vardas #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.