#Ethiopia | መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዘንድ ሕጋዊ ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቀ የመጀመሪያው የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም መሆኑን አስታወቀ።
የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጌትነት ሃይሌ እንደገለጹት፣ ይህ ታሪካዊ ምዝገባ ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ሲያከናውናቸው የቆዩትን መልካም ስራዎች እና የዕድገት መስመሮች የበለጠ ለማሳደግ፣ ለማስፋፋትና አቅሙን አጠናክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ተነሳሽነትን ይፈጥርለታል።
አቶ ጌትነት አክለውም በካፒታል ገበያው አማካኝነት ተጨማሪ ኢንቨስትመንት በመሳብ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንደሚቻል ጠቁመው፣ ይህም የተገኘውን ካፒታል በመጠቀም በከተማና በገጠር የሚገኙ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን፣ አነስተኛ አምራቾችን እና አቅም የሌላቸውን ዜጎች በስፋትና በጥራት ተዳራሽ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።
በተጨማሪም በተደረገው የህግና የፋይናንስ ምዝገባ ሂደት ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶች ያጋጠሙ ቢሆንም፣ ከሚመለከታቸው የመንግስትና የፋይናንስ ተቋማት ጋር በተደረገ ቅንጅታዊ ጥረት እንቅፋቶችን ማለፍ መቻሉን ገልጸው፣ በቀጣይም ተቋሙ የአክሲዮን ሽያጭ በማካሄድ፣ የቅርንጫፍ ተደራሽነቱን በመጨመር እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በመተግበር ጠንክሮ እንደሚሰራ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በሌላ በኩል የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አዜብ ማሞ እንደገለጹት፣ ተቋሙ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን የተሻለ ደረጃ ለማድረስ አምስት ቅርንጫፎችን ከፍቶ በብድር አሰጣጥና በቁጠባ አሰባሰብ ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።
በጌትነት ተመስገን
#MebaeMicrofinance #EthiopianCapitalMarket #MicrofinanceET #CapitalMarketET #EthiopianEconomy #FinancialInclusion #InvestInEthiopia #Ethiopia




Source: GetuTemesgen









No comments yet.