ሴንትራል ያማረች ሆቴል በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ የንግድ እውቅና እና ሽልማት ተበረከተለት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሀዋሳ ከተማ በ2018 ዓ.ም በታማኝነትና በቅንነት ሸማቹን፣ ሀገርን እና መንግስትን በማገልገል አርአያነቱን ያስመሰከረው ሴንትራል ያማረች ሀዋሳ ሆቴል ከከተማው ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የሰርተፍኬትና የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት አግኝቷል።

በተጨማሪም ሆቴሉ በዘርፉ ባሳየው የላቀ አገልግሎት ልዩ ተሸላሚ በመሆን የዋንጫ እና የሜዳሊያ እውቅና ከሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ተበርክቶለታል።

ይህንን ከፍተኛ እውቅና የሴንትራል ያማረች ሀዋሳ ሆቴል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ፍትህ ወልደሰንበት ከከንቲባው እጅ ተቀብለዋል።

የሆቴሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ፍትህ ባደረጉት ንግግር፣ ለተከናወኑ ስራዎች የሚሰጥ እውቅና ለበለጠ ትጋት የሚያነሳሳ መሆኑን ገልፀው፣ የእናታቸው የወይዘሮ አማረች ዘለቀን የበጎ ስራ ውርስና አሰረ ፍኖት በተገቢው መንገድ ለማስቀጠል እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።

#Hawassa #CentralYamarachHotel #EthiopiaBusiness #HotelIndustry #BusinessExcellence #Sidama #EthiopiaNews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1