በሳር ማጨድ ቤተሰቡን እየረዳ ያለ የ12 አመቱ ታዳጊ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኮለምበስ ጆርጂያ የ12 ዓመቱ ታዳጊ በዕረፍቱ የጀመረው የሳር ማጨድ ሥራ ለቤተሰቡ ድጋፍ የሚሆን ገቢ እያገኘ ይገኛል።

የ12 ዓመቱ ጄይደን ጃክሰን በዕረፍቱ ወቅት እንደ ቀልድ የጀመረው የሳር ማጨድ ስራ ወደ ቤተሰቡን በገቢ እንዲረዳ አስችሏል።

ዓላማው ገንዘብ ማግኘት ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡን ማገዝ ነው።

ሀሳቡ የተጀመረው ባልተጠበቀ ሁኔታ ነበር።

ጄይደን የሳር ማጨጃውን እየገፋ በጎዳና ላይ ሲራመድ አንድ ግለሰብ የቤቱን ግቢ እንዲያጸዳለት ጠየቀው።

እሱም በሃሳቡ ተስማምቶ ሥራውን አከናወነ ያ የመጀመሪያ ሥራውም በፍጥነት ለሌሎች እድሎች በር ከፈተለት።

የሳር ማጨድ አገልግሎቱን የሚያስተዋውቅ የፌስቡክ መልእክት ከ100 ጊዜ በላይ በማጋራት ከአካባቢው በርካታ ደንበኞችን እንዲያገኝ አስችሎታል።

በቅርቡ በትሩዝ ስፕሪንግ አካዳሚ የአምስተኛ ክፍል ትምህርቱን ያጠናቀቀው ጄይደን የሳር እንክብካቤ ሥራን ቀድሞውኑ ይወደው ነበር።

እናቱ እንደተናገረችው ስለ ሳር ማጨድ እና አረም ማጽዳት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ቪዲዮዎችን ዘወትር ይመለከት ስለነበር ሥራውን በፍጥነት መላመድ ችሏል ብላለች።

ከስድስት ልጆች ሁለተኛ ልጅ የሆነው ጄይደን ከሥራው የሚያገኘውን ገቢ የትምህርት ቁሳቁሶችን እና አልባሳትን ለመግዛት እንዲሁም ታናናሾቹን ለመደገፍ አቅዷል።

የእሱ ታሪክ ሳር ከማጨድ በላይ ትርጉም ያለው ሆኗል።

ይህም በትጋት በኃላፊነት ስሜት እና ለመረዳዳት በሚደረግ ፍላጎት ቀላል የእረፍት እንቅስቃሴን ወደ ትልቅና ትርጉም ወደ ያለው ስኬት መለወጥ እንደሚቻል አሳይቷል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Jackson #Columbus
#summer #cuttinggrass
#neighborhood #advertising


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: