በፊላዴልፊያ የምድር ውስጥ ባቡር ጣቢያ ሰዎችን ሲያስደነግጥ የነበረው ጭንብል ለባሹ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአሜሪካ ፔንስልቬንያ ግዛት ፊላዴልፊያ ከተማ ባቡር ጣቢያዎችና መንገዶች ላይ አስፈሪ የህፃን አሻንጉሊት (Chucky-style) የፊት ጭንብል በማድረግ መንገደኞችን ሲያስደነግጥ፣ ሲያሳድድ እና ስጋት ሲፈጥር የነበረ ግለሰብ ያልተጠበቀ የመልስ ምት ገጥሞታል።

በኒውዮርክ ታይምስ እና በበርካታ የዓለም አቀፍ ዜና አውታሮች ሽፋን በተሰጠው በዚህ ክስተት፣ ተጠርጣሪው በከተማዋ ለጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በርካታ ሰዎችን ለማስፈራራት ቢሞክርም፣ በመጨረሻ ግን ያልተጠበቀ ድፍረት ካሳየች ሴት ጋር ተፋጧል።

ተጠርጣሪው የሞባይል ስልኩን መብራት በማብራት ድርጊቱን በቪዲዮ እየቀረጸ ሰዎችን ሲያሳድድ እና “ልትሞች ዝግጁ ነሽ?” የሚሉ የማስፈራሪያ ቃላትን ሲናገር እንደነበር የፊላዴልፊያ ፖሊስ ገልጿል።

ጃሜካ ቪልሰን (Jameka Wilson) የተባለችው ሴት ግለሰቡ ሊያሳድዳት ሲሞክር ከመሸሽ ይልቅ ፊቷን ወደ እሱ በመመለስ “እሺ፣ እንጋጠም!” በማለት የውጊያ ዝግጅት አድርጋለች።

በመቀጠልም ደረቱ ላይ በርግጫ በመምታቷ ተጠርጣሪው ተሰናክሎ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ከአካባቢው ለማምለጥ ተገዷል።

የፊላዴልፊያ ፖሊስ መምሪያ (Philadelphia Police Department) ክስተቱን በCCTV ካሜራዎች በመከታተል ተጠርጣሪውን ዚማየር ሂውስ (Zymire Hughes) በማለት የለየው ሲሆን፣ በህዝብ ደህንነት ላይ ስጋት በመፍጠር፣ ህገ-ወጥ ማስፈራራት እና ጥቃት በመሰንዘር ወንጀሎች ህጋዊ እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#GetuTemesgen #GetuTemesgenMedia #Philadelphia #PhillyNews #USNews #BreakingNews #SubwayIncidents #SelfDefense #CrimeNews #PhiladelphiaPolice #NYTimes #WorldNews #TrendingNews


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: