ነገ ቅዳሜ በመቀሌ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የአሽንዳ ዓመታዊ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሠረዘ። የአሸንዳ በዓል ማስጀመሪያ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ነገ ቅዳሜ በመቀሌ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የአሽንዳ ዓመታዊ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሠረዘ።
የአሸንዳ በዓል ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት የተሠረዘው፣ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄደው የድሮን ጥቃት ሳቢያ መኾኑን የትግራይ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጧል።
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አንቂዎች፣ በክልሉ በሴቶች ላይ የሚፈጸመሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በመቃወም ሴቶች በዓሉን ጥቁር በመልበስና “ጥቁር አሸንዳ” በሚል መሪ ቃል እንዲያከብሩት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር።
ይህንኑ ተከትሎ፣ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ከመደበኛው ባሕላዊ ስነ ሥርዓት ውጪ ሌላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም ሲል ሰሞኑን ማስጠንቀቂያ አውጥቶ እንደነበር አይዘነጋም።

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: