#Ethiopia | ራሱን ማዳን ያልቻለ በአላፊ አግዳሚው ተስፋ ተቆርጦበት ጎዳና ላይ የተጣለ አንድ ውሻ የኋላ ኋላ የሰው ልጅ ሕይወት ያድናል ብሎ ማን ገመተ?
ኖርማን ይባላል የመጀመሪያ ሕይወቱ በብቸኝነትና በችግር የተሞላ ነበር።
በጎዳና ላይ ተጥሎ ከቆየ በኋላ ወደ እንስሳት መንከባከቢያ ማዕከል እንዲገባ ተደረገ።
በዚያም አኔት እና ስቲቭ ማክዶናልድ የተባሉ ደግ ባልና ሚስቶች ጉልበቱን አይተው አሳደጉት።
ነገር ግን ደስታቸው ብዙ አልዘለቀም ብዙ ሳይቆይ ኖርማን በድንገት እንስሳትን በሚያጠቃ የዓይን ሕመም ምክንያት ሙሉ በሙሉ እይታውን አጣ።
ዓለሙ በጨለማ ተዋጠች።
ነገር ግን በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት በተከሰተው አስገራሚ አጋጣሚ ይህ ዓይነ ስውር ውሻ የብዙዎችን አፍ ያስያዘ ተአምር ሠራ።
ሊዛ የተባለች ታዳጊ ሴት ጥልቀት ባለው ውሃ ውስጥ ገብታ በሞትና በሕይወት መካከል ሆና “እርዱኝ!” እያለች ትጮህ ነበር።
በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በድንጋጤ ተጨነቁ በዚህ መሀል እይታውን ያጣው ኖርማን ግን ቅጽበታዊ ውሳኔ ወሰነ።
ኖርማን ልቡና ጆሮዎቹ ትክክለኛውን የልጅቷ አቅጣጫ ጠቆሙት።
ኖርማን ለህይወቱ ምንም ሳይሰጋ ወደ ጥልቁ ውሃ ውስጥ በመግባት የጩኸቱን አቅጣጫ ተከተለ።
ውቅያኖስ የሚመስለውን ውሃ እየቀዘፈ ሊዛ ዘንድ ደረሰ።
ሊዛ በፍርሃት ተውጣ ኖርማንን አጥብቃ ያዘችው።
ዓይነ ስውሩ ውሻ የሴት ልጅቷን ሕይወት ተሸክሞ ከዳር የሚመጣውን የሰዎች ድምፅ እንደ መሪ ኮምፓስ በመጠቀም ሊዛን ከሞት አተረፋት።
አንድ ጊዜ በሰው ልጅ ተጥሎ የነበረ በኋላም ዓይነ ስውር የሆነ ውሻ በአስቸጋሪው ሰዓት ግን የሰውን ልጅ ሕይወት ለማዳን ብቸኛውና ትክክለኛው መሪ እሱ ሆነ።
ኖርማን ማየት አይችልም ነበር እርዳታ የሚፈልግ የነፍስ ጥሪ ሰምቶ በደመ ነፍስ የተመራ እውነተኛ የዘመናችን እውነተኛው ጀግና ውሻ እንዲባል አስገድዷል።
ይህ ፊልም አይደለም ይልቁን የአንድ እውነተኛ ውሻ የጀግንነት ታሪክ እንጂ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#America #Oregon
#blind #rescue #dog
#teenagegirl #Norman
Source: GetuTemesgen









No comments yet.