የመንግስት ት/ቤቶች የትምህርት ጥራት የግሎቹን ከስራ እያስወጣ ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሩዋንዳ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጥራት መጨመር ከ30 በላይ የግል ትምህርት ቤቶችን ከገበያ ውጭ አደረገ።

በሩዋንዳ በግል ባለሀብቶች የተያዙ ከ30 በላይ ትምህርት ቤቶች በቂ ተማሪ ባለማግኘታቸው ስራቸውን በዘላቂነት ለማቆም ተገደዋል።

ለበርካታ አስርት ዓመታት ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት የበላይነቱን ይዘው የቆዩት የግል ትምህርት ቤቶች የመንግስት ትምህርት ቤቶች ባሳዩት ከፍተኛ የጥራት እድገት ምክንያት ተማሪዎቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እያጡ ይገኛሉ።

መንግስት በትምህርት ዘርፉ ላይ ባደረገው አዲስ ኢንቨስትመንት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ከግል ወደ መንግስት ትምህርት ቤቶች እየፈለሱ ይገኛሉ።

የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር የገጠመውን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመቋቋም መንግስት ለተማሪዎች ድጎማ በማድረግ በግል ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ እንዲያደርግላቸው እና ድጋፍ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ነገር ግን የሩዋንዳ ትምህርት ሚኒስቴር የቀረበለትን የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።

ሚኒስቴሩ የህዝብ ግብር የሚወጣው የመንግስትን የትምህርት መሠረተ ልማት ለማስፋፋትና ለማሻሻል ብቻ መሆኑን በመግለጽ የግል ተቋማት በገበያ ውድድር ውስጥ እራሳቸውን ችለው መቆም እንዳለባቸው አስታውቋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Rwanda #government
#private #schools
#Education #quality


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: