#Ethiopia | አሊያ ቢፍቱ ቃሌ ትባላለች። ላለፉት 9 ዓመታት ኑሮዋን ለማሸነፍ በሱዳን ካርቱም የቆየች እህታችን፣ በሱዳን ባለው ጦርነት ምክንያት ተፈናቅላ የተለያዩ ጉዳቶች ደርሰውባታል።
በመተማ የሚገኘው IOM ከለላ አድርጎላት ቆይቷል። ባጋጠማት የአዕምሮ ህመም ምክንያት ህክምናዋን ለማስተናገድ ምቹ ሁኔታ ስላልነበር፣ ተቋሙ ከማዕከላችን ጋር ባለው መልካም ግንኙነት ጎንደር ወደሚገኘው “ካለን ብናካፍል” እንድትመጣ ተደርጓል።
ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ በተደረገላት አስፈላጊ ህክምናና እንክብካቤ፣ አሁን ላይ ነገሮችን በማስታወስ መናገር ችላለች።
በዚህም መሠረት ትውልድና እድገቷ በኦሮሚያ ክልል፣ ገደብ አሳሳ ከተማ መሆኑን ገልጻለች።
የቤተሰቦቿ ስም፦
እናቷ፡ ወ/ሮ መዲና ሀሱ ደለቁ
ወንድሞቿ፦
• የሱፍ ቢፍቱ
• አህመድ ቢፍቱ
• ሀጂ ቢፍቱ
• መሀመድ አዎል ቢፍቱ
እህቶቿ፦
• ሙኩ ቢፍቱ
• አሚና ቢፍቱ
• ሲምባ ቢፍቱ
ቤተሰቦቿ ያለችበትን እንዲያውቁ እና እሷም ከናፈቀቻቸው ቤተሰቦቿ ጋር እንድትገናኝ፣ ይህ መልዕክት ለሚመለከተው ሁሉ እንዲደርስ ጥሪ እናቀርባለን።
ለበለጠ መረጃ፦
09 18 82 82 00
09 41 02 03 04
ካለን ብናካፍል የህፃናት፣ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህመም መረጃ ማዕከል
እባክዎ ለቤተሰቦቿ እንዲደርስ Share ያድርጉ!


Source: GetuTemesgen









No comments yet.