ያንጎ ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ ያለውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ተጠቃሚነት ይበልጥ አስፋፋ!

- Advertisement -
Sidebar AD

ያንጎ ኢትዮጵያ ባደረገው ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት፣ 50 ቢዋይዲ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ነሐሴ 2018ዓ.ም. – የዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ኢትዮጵያ፣ 50 አዳዲስ ቢዋይዲ ኢ2 ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት፣ በአዲስ አበባ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አማካኝነት የሚመጣውን አገልግሎት አስፋፍቷል። ተሽከርካሪዎቹ በኮምፎርት ፕላስ (Comfort+) ምድብ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ ሲሆን፣ የተሽከርካሪ መኪኖች አቅራቢ ከሆነው ኤለጋንስ አስመጪና ላኪ ፒኤልሲ ጋር በመተባበር ወደ ያንጎ ጉዞ የትራንስፖርት አገልግሎት መድረክ የተቀላቀሉ ናቸው። ለዚህ ፕሮጀክት፣ የገንዘብ ድጋፍ የተገኘው ከዳሽን ባንክ ሲሆን በጠቅላላ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ኢንቨስትመንት ወጪ ተደርጎበታል።

አዲሶቹ ተሽከርካሪዎች በዋና ከተማዋ ውስጥ፣ አስተማማኝና ምቹ የመጓጓዣ አገልግሎት ለሚፈልጉ የንግድ ተጓዦች፣ የድርጅት ደንበኞች እና ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የኮምፈርት ፕላስ ጉዞዎችን ከጥራት ጋር ተደራሽ ያደርጋሉ።

ይህ የአገልግሎት ማስፋፊያ ሥራ፣ በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ በያንጎ ጉዞ የአገልግሎት መድረክ ላይ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መጠን ከ15 በመቶ በላይ የሚያደርስ ሲሆን ከተማዋ ወደ የበለጠ ንጹህና ዘላቂ የከተማ መጓጓዣ ሥርዓት እንድትሸጋገር ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።

ይህ የማስፋፊያ ሥራ፣ ተሽከርካሪዎችን ወደአገልግሎት መድረኩ ከማስገባት ያለፈ ሚና ያለው ተግባር ነው። በሦስቱ ወገኖች መካከል የተፈጠረው አጋርነት፣ ማለትም የቴክኖሎጂ መድረክን፣ የአገር ውስጥ የተሽከርካሪዎች አስመጪን እና የፋይናንስ ተቋምን በማስተባበር የተሠራው ትልቅ ሥራ፣ የተሽከርካሪ ኢንቨስትመንትን ከዚህም በላቀ ደረጃ ተግባራዊና ዘላቂ ማድረግ እንደሚቻል ያሳያል። ይህም በመላው ኢትዮጵያ ላሉ ሥራ ፈጣሪዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ሊደገም የሚችል የኢንቨስትመንት ሞዴል ምሳሌን ይፈጥራል።

በያንጎ፣ የኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር የቀናለም አበበ በመግለጫው ላይ “የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አገልግሎትንና ተደራሽነትን በማስፋፋት የጉዞ አገልግሎቶችን ጥራት እያሻሻልን በተጨማሪም ለተሽከርካሪ አስመጪዎችና ሻጮች በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንዲችሉ አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠርን ነው። ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን ሥራ ፈጣሪዎችን የሚደግፍ እና በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ዕድገትን የሚያግዝ ሞዴል እያመቻቸን ነው።” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኤለጋንስ አስመጪና ላኪ ፒኤልሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ቶፊቅ መሐመድ በበኩላቸው “ከያንጎ ጋር ያለን አጋርነት፣ ከዳሽን ባንክ ካገኘነው የፋይናንስ ድጋፍ ጋር ተደምሮ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የማስገባት ዐቅማችንን እንድናሳድግ እና ለተሳፋሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው የጉዞ ልምድ እንድናቀርብ አስችሎናል። ይህ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ ላሉ የተሽከርካሪ አስመጪና ሻጮች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ያላቸውን የንግድ ዐቅም በሚገባ ያሳያል።” ብለዋል፡፡

የያንጎ የገበያ ጥናትና ዳሠሣዎች፣ የአስተማማኝ እና ዘላቂ የመጓጓዣ አገልግሎት ፍላጎት፣ በአዲስ አበባ በተለይም በድርጅቶች እና በዓለም አቀፍ ተጓዦች ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ። ያንጎ ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መጓጓዣን ለማስፋፋት ምቹ የሆኑ አማራጮችን በመፈለግና በመመርመር ከተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ ከሥራ ፈጣሪዎች እና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በትብብር መሥራቱን ይቀጥላል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: