ዌብስፕሪክስ የተሰኘዉ ግዙፍ የኢንተርኔት አገልግሎት፤ ክላዉድና ሰርቨር አቅራቢ ድርጅት ሰራተኞች እስከዛሬ ነሃሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሐምሌ ወር ደመወዝ አልተከፈላቸዉም።
ስማቸዉ እና ማንነታቸዉ እንዳይገለጽ የጠየቁ የድርጅቱሰራተኞች ባደረሱን መረጃ፤ 85 የድርጅቱ ሰራተኞች የሃምሌ ወርደመወዝ ስላልተከፈለቸዉ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዋል ብለዋል።
በተለመደዉ ድርጅታዊ አሰራር መሰረት ዌብስፕሪክስ፤ በፈረንጆችቆጣጠር በየወሩ መጨረሻ ቀን ድረስ ወርሃዊ ክፍያ ሳያዛንፍይከፍል ነበር። በዚህ አሰራር መሰረትም ድርጅቱ የሃምሌ ወርደመወዝን ሃምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም (ጁላይ 31 ቀን 2026)ለሰራተኞቹ መክፈል ነበረበት።
ሆኖም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዛሬ ነሃሴ 15 (ኦገስት 21 ቀን2026) ድረስ ሰራተኞች የሃምሌ ወር ደመወዝአልተከፈላቸዉም።
አንድ ሰራተኛም፤ “የኑሮ ዉድነቱ አልቀመስ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ለአንድ የወር ደመወዝተኛ ደመወዝ መከልከል፤ ለሞት አሳልፎየመስጠት ያህል ጭካኔ ነዉ” ብለዋል።
ብዙዎቹ የድርጅቱ ሰራተኞች የቤት ኪራይ ለመክፈልመቸገራቸዉንና የቤት አስቤዛ ለማሟላት ጭምር እጅእንዳጠራቸዉም በምሬት እና በከፍተኛ ሀዘን ዉስጥ ሆነዉ አስረተድተዋል።
ከድርጅቱ ሰራተኞች ባገኘነዉ መረጃ መሰረት፤ ዌብስፕሪክስለሰራተኞቹ ደመወዝ መክፈል ያልቻለዉ ፤ በገንዘብ እጦት ወይምአቅም ማነስ አይደለም። ለደመወዝ አለመከፈል ምክንያት የሆነዉበድርጅቱ ባለ አክሲዮኖች መካከል የተፈጠረዉ እርእ በእርስአለመግባባት ነዉ።
ያገኘናቸዉ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፤ የዌብስፕሪክስ ባለአክሲዮን በሆኑት፤ አቶ አበባዉ ደስታ፣ አቶ አብርሃምምንዉየለት፣ አቶ መቅደስ አክሊሉና አቶ ዳዊት ብርሃኑ መካከልለወራት የዘለቀ አለመግባባት ተፈጥሯል።
የባለ አክሲዮኖቹ አለመግባባት መንስኤም፤ ድርጅቱን በበላይነትከመጠቅለል፤ መቆጣጣር እና የመምራት ፍላጎት የመነጨመሆኑን ነዉ መረጃዎች የሚያሳዩት።
ይህ ድርጅቱን በብችኝነት የመጠቅለል ፍላጎት በሶስቱ ባለአክሲዮኖች ማለትም፤ አቶ አበባዉ ደስታ፣ አቶ አብርሃምምንዉየለት እና አቶ መቅደስ አክሊሉ በኩል እየከረረ መጥቶ፤ የድርጅቱን መስራች፤ ባለከፍተኛ ድርሻ እና ዋና ስራ አስፈፃሚአቶ ዳዊት ብርሃኑን ከድርጀቱ እስከማስናበት መድረሱንምሰምተናል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት አቶ አበባዉ ደስታ፣ አቶ አብርሃምምንዉየለት እና አቶ መቅደስ አክሊሉ በመመሳጣር እና መተባበር፤ የድርጅቱን መስራች እና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳዊት ብርሃኑንከኃላፊነት እንዲነሱ ከወሰኑ በኋላ፤ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚየነበሩትን አቶ አብርሃም ምንዉይለት ድርጅቱን እንዲመሩ በዋናስራ አስፈፃሚነት ሾመዉ ነበር።
አቶ አብርሃምም ከሰኔ 08 እስከ ሃምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ምድርጅቱን በዋና ስራ አስፈፃሚነት ከመሩ በኋላ፤ አቶ ዳዊት ከዋናስራ አስፈፃሚነት የተነሱበት ዉሳኔ እና ቃለ ጉባኤ ፤ የድርጅቱንህገ ደንብ የጣሰ ነዉ በሚል በፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዳይፈፀምበመታገዱ፤ ከሃምሌ 27 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ዳዊት ወደሃላፊነት ተመልሰዋል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዚህ ወዝግብ ሂደት ነዉ፤ የዌብስፕሪክስ ሰራተኞች የሃምሌ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸዉ። ዌብስፕሪክስን ለአንድ ወር ከ15 ቀን ያስተዳደሩት አቶ አብርሃምምንዉየለት፤ የሰኔ ወር ደመወዝን እንደከፈሉት ሁሉ የሃምሌንምወር የሰራተኞች ደመወዝ መክፈል እየቻሉ፤ ሳይፈፅሙት ቀርተዋል።
አቶ ዳዊት ወደ ሃላፊነት ከተመለሱ በኋላ፤ የድርጅቱን የፋይናንስሃላፊ አቶ አብነት ደምሴን የሰራተኞቹ ደመወዝ ለምንእንዳልተከፈለ ማብራሪያ በመጠየቅ፤ ክፍያዉ በአስቸኳይእንዲፈፀም ትእዛዝ ቢያስተላልፉም፤ አቶ አብነት ደምሴ፤ትእዛዙን ለመፈፀም ፈቃደኛ አልሆኑም።
በዚህም ምክንያት አቶ አብነት ለተወሰኑ ቀናት ከስራ ከታገዱበኋላ፤ ሰሞኑን ሙሉ በሙሉ ከድርጅቱ እንዲሰናበቱ ተደርጓል።
ከዚህ ሂደት በኋላ የዌብስፕሪክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳዊት፤ አስቅድመዉ፤ የድርጅቱ ሰራተኞች ደመወዝ የሚከፈልበትአቢሲኒያ ባንክን፤ ለሰራተኞች ደመወዝ እንዲለቅ ቢጠይቁም፤ ባንኩ ከፍርድ ቤት የመጣዉ ትእዛዝ፤ ለገንዘብ እንቅስቃሴየመፈረም ስልጣኑን፤ ለአቶ ዳዊት ወይም አቶ አብርሃምመሰጠቱን በግልጽ ስላማያሳይ ደመወዝ ለመክፈል እንቸገራለንየሚል ምላሽ በመስጠቱ ለሰራተኞቹ ደመወዝ መክፈልአልተቻለም።
ቀጥሎም አቶ ዳዊት በተመሳሳይ መልኩ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክተቋሙ ካለዉ ተቀማጭ ገንዘብ ላይ ለሰራተኞቹ ደመወዝእንዲከፍል ጠይቀዉ ነበር። ሆኖም ባንኩ ለዌብስፕሪክስ ምክትልዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም፤ ጉዳዩን ሲያሳዉቃቸዉ፤ ምንም አይነት ክፍያ ብትፈፅሙ፤ ባንኩን እከሰዋለሁ የሚል ምላሽበመስጠታቸዉ፤ አሁንም ደመወዝ የመክፈል ሙከራዉ ሳይሳካቅርቷል።
በዚህ መካከል የሃምሌ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸዉየዌብስፕሪክስ ሰራተኞች በከፍተኛ ችግርና እና እንግልት ዉስጥሆነዉ ደመወዛቸዉን እየተጠባበቁ ይገኛሉ። የድርጅቱ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ዳዊት ብርሃኑም፤ ሰራተኞቹን ሶስት ጊዜ ሰብስበዉበማናገር፤ ያለዉን ሁኔታ በዝርዝር ማስረዳታቸዉን አረጋግጠናል። የሰራተኞቹ የደመወዝ ክፍያ ጉዳይ ፍርድ ቤት የደረሰ ሲሆን፤ ዛሬአርብ ነሃሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም እልባት እንሚያገኝም ይጠበቃል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ በአቶ ዳዊት ብርሃኑ የተመሰረተዉ ዌብስፕሪክስ ከ30 ሺህ በላይ የኢንተርኔት ደንበኞች ያሉት፤ ከ5 በላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን የኢንተርኔት እና ክላዉድአገልግሎት የሚያቀርብ፤ ትልልቅ የባንክ ቅርንጫፎች የሚገናኙበት የኔትወርኪንግ አገልግሎት ያቀረበ፤ እንዲሁም የሁለት የመንግስት ሚዲያዎችን የቀጥታ ስርጭት የሚያስተናግድ ግዙፍ ድርጅት ነዉ።


Source: Yeneta Tube









No comments yet.