የሳዲዮ ማኔ :

- Advertisement -
Sidebar AD

ግዙፍ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ፓርክ

#Ethiopia | የሴኔጋሉ የእግር ኳስ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ ከስፖርቱ ዓለም ባሻገር በሀገሩ ደቡባዊ ክፍል ካሳማንስ በሚገኘው ባምባሊ አካባቢ ግዙፍ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ማቀዱን ይፋ አድርጓል።

ይህ ታላቅ የልማት ፕሮጀክት በፍራፍሬ ምርት እና በግብርና ውጤቶች ማቀናበር ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ ሲሆን ለቀጣናው ወጣቶች እስከ 2ሺህ 500 የሚደርሱ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

የማኔ Initiative በርካታ አፍሪካውያን ስፖርተኞች ያፈሩትን ሀብት የግል ንብረት ብቻ ከማድረግ ይልቅ ወደ ሀገራቸው በመመለስ ለህብረተሰባቸው ዘላቂ የስራ እድል እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን በሚፈጥሩ ስራዎች ላይ የማዋል በጎ ልማድ አካል ነው።

ለሳዲዮ ማኔ መልእክቱ ግልጽ ነው፤ እግር ኳስ ጊዜያዊ ስምና ዝናን ሊያስገኝ ይችላል፤ በሰዎች እና በግብርና ዘርፍ ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ግን የነገዋን አፍሪካ ብሩህ ተስፋ ይገነባል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#SadioMane #Senegal #Africa #Agriculture #EyeGambia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: