መስማት የተሳነው የኡበር አሽከርካሪ ያስቀመጠው መልእክት…

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በለንደን መስማት የተሳነው የኡበር አሽከርካሪ ያስቀመጠው መልእክት የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

በእንግሊዝ ለንደን የሚኖረውና መስማት የተሳነው ኦኑር ከረይ የተባለው የኡበር አሽከርካሪ ከተሳፋሪዎቹ ጋር ለመግባባት ባዘጋጀው ድንቅ መልእክት ምክንያት በሶሻል ሚዲያ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፎለታል።

ኦኑር ተሳፋሪዎች በሚያወሩበት ወቅት መልስ የማይሰጣቸው ለምን እንደሆነ እንዲረዱት ከመንገደኛ ወንበር ጀርባ አንድ ማስታወሻ ለጥፏል።

ማስታወሻውም ተሳፋሪዎች መልእክት በስልክ አጭር ጽሑፍ መላክ እንደሚችሉ ወይም መኪናው በቆመበት ወቅት ማስታወሻ ደብተር መጠቀም እንደሚችሉ የሚያብራራ ነው።

ነገር ግን የብዙዎችን ቀልብ የሳበውና መልእክቱን ልዩ ያደረገው ሌላው ዝርዝር ነገር ነው ኦኑር ተሳፋሪዎች የራሳቸውን ሙዚቃ በAUX አማካኝነት ማጫወት እንደሚችሉ ገልጾ ሙዚቃው ቤዝ ካለው እሱም ቢሆን ስሜቱን እንደሚያጣጥመው ገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#England #London
#deaf #Uberdriver
#technology #customers


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: