“አሸንዳ ለሰላም” በሚል መርህ ቃል በVIP CLUB፣ VIP EVENT እና ሚላኖ ሆቴል ትብብር የተዘጋጀው ታላቅ የሙዚቃና የመዝናኛ ዝግጅት ከነሐሴ 16 እስከ 18 ቀን በአዲስ አበባ በAddis International Convention Center ይካሄዳል።
ዝግጅቱ የአሸንዳን በዓል ከሰላም፣ አንድነት እና ደስታ ጋር ለማክበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከ20 በላይ አርቲስቶችና ዲጄዎች በመድረኩ ላይ እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
በዝግጅቱ ላይ ራሄል ሃይለ፣ ተስፋአለም ቆርጫጭ፣ ሳሚ ዳን፣ ዮማርዮስ፣ DJ ሚላ፣ ኪሮስ ኤሊዛ፣ ዮሳን ጌታሁን፣ ዛፉ ኪሮስ አለማዬ፣ ስዩመቃል ገብሬ፣ ሙልጌታ ማሉዳ፣ ሃለዋት ሓጎስ፣ መኣዛ ዮሃንስ፣ ፊልሞን በቀለ፣ ግዛቸው ሰሎሙን፣ ፊልሞን ካሕሱ፣ ኪስማው፣ እምብዛ አሊጋዝ፣ ማህደር ጌታሁን፣ ጆን ሃፍቱ እና ሶፍያ አፅበሃ እንደሚታደሙ ተገልጿል።
የዝግጅቱ ትኬት ባርኮዱን ስካን በማድረግ ወይም በተሰጠው ሊንክ በመግባት መግዛት የሚቻል ሲሆን፣ ትኬቶቹ በቦሌ VIP Club፣ በ22 VIP Club እና በሰሚት አካባቢ በሚገኙ የተለያዩ የምግብ ቤቶችና የትኬት መሸጫ ቦታዎች እንደሚገኙ እና የትኬቶቹም ዋጋ ኖርማል 2000 ብር በር ላይ 2500 ብር VIP 4000 ብር VVIP 7000 መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
የአሸንዳን በዓል በሙዚቃ፣ በደስታና በአንድነት ለማክበር የተዘጋጀው ይህ ዝግጅት በርካታ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል።


Source: FastMereja








No comments yet.