የልጅነት ህልሟን እውን በማድረግ የቅመማቅመም ዝግጅትን ወደ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ ያሸጋገረችው ስኬታማ ባለሀብት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በወይዘሮ ሔዋን ቀለመወርቅ ባለቤትነት በደብረ ብርሃን ከተማ የተቋቋመው ሔዋን ስፓይስ ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካ ስራ በመጀመር ከ30 በላይ የሆኑ የተፈጥሮ የሀገር ውስጥ የቅመማቅመም ምርቶችን በማቀነባበር ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያዎች ማቅረብ ጀምሯል።

በ730 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተገነባው ይህ ዘመናዊ ፋብሪካ መነሻ ሀሳቡ የተገኘው የወይዘሮ ሔዋን እናት ከሚያሳዩት ጠንካራ የሰራተኝነት ህይወት እንደሆነ ይነገራል።

እናቷ በድንጋይ ወፍጮ እየፈጩ ለገበያ ያቀርቡ የነበረውን አድካሚ ስራ ልጃቸው ሔዋን በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሰራር በመተካት የእናቷን ስም እና ጥረት ማስከበር ችላለች።

ፋብሪካው እንደ በርበሬ፣ ሚጥሚጣ፣ ሽሮ ያሉ በርካታ የሀገር ውስጥ ምርቶችን በከፍተኛ ንጽህና አዘጋጅቶ ያቀርባል።

ከተለያዩ የሀገር ውስጥ ማሰራጫዎች በተጨማሪ ምርቶቹን በዱባይ፣ ቶሮንቶ፣ ለንደን፣ ኒውዮርክ እና በአማዞን በኩል ለውጭ ሀገር ገበያ በማቅረብ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ይሰራል።

ተቋሙ በሙሉ አቅሙ ማመርት ሲጀምር በሰዓት 2 ቶን እንዲሁም በወር እስከ 1 ሺህ 440 ቶን ማቀነባበር እንደሚያስችል ተገልጻል።

#DebreBerhan #HewanSpice #EthiopianAgroProcessing #Entrepreneurship #LocalProducts #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1