#Fastmereja:-የመጪውን የ2019 አዲስ ዓመት አስመልክቶ በሴንቸሪ ፕሮሞሽን እና ኤቨንትስ አዘጋጅነት የሚከናወነው 35ኛው «ዘመን ገበያ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ» በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል በይፋ ተከፈተ።
ከዛሬ ነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ ታላቅ የንግድ ትርኢትና ባዛር፤ ከ500 በላይ አምራቾችን፣ አስመጪና ላኪዎችን፣ የንግድ ወኪሎችን እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ያሳተፈ ነው።
በዚህ ኤክስፖ ህብረተሰቡ በቂ ጊዜ አግኝቶ በተረጋጋ ሁኔታ ግብይትና እረፍቱን እንዲያሳልፍ ሲባል የመጎበኛና የግዢ ሰዓቱ ከጠዋቱ 2:30 እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ እንዲራዘም የተደረገ ሲሆን ተሳታፊ አጋር ድርጅቶችም ለህብረተሰቡ ተመጣጣኝ ዋጋና ልዩ ቅናሽ ለማቅረብ መስማማታቸዉ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት የንግድ እንቅስቃሴው በይፋ የተጀመረ ሲሆን፤ ከነገ ነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ እስከ ኤክስፖው ማጠናቀቂያ ድረስ በየቀኑ የሚካሄዱ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ይጀምራሉ።
በተለይም እስከ ነሐሴ 21 ቀን ድረስ የአሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላትን የሚያደምቁ ልዩ የባህል ጭፈራ መርሃ-ግብሮች ለታዳሚዎች የሚቀርቡ ይሆናል።
ታዳሚዎች የመግቢያ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት በቀላሉ መቁረጥ የሚችሉ ሲሆን፤ በጳጉሜ 5 ቀን ምሽት በሚወጣው ዕጣ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶሞቢል፣ የBMW ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል እና ብስክሌት በሽልማት የሚያገኙ ይሆናል።



Source: FastMereja







No comments yet.