አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ በናይሮቢ ተሸኙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የናይሮቢ ቢሮዎች የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ክቡር አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ የሥራ ዘመናቸውን በማጠናቀቃቸው ምክንያት በናይሮቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ደማቅ የሽኝት መርሃ-ግብር ተከናወነላቸው።

ኤምባሲው ከዲያስፖራ ማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኬንያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከአምሳ በላይ ሀገራት የተውጣጡ አምባሳደሮች እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል።

​በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የዲፕሎማቲክ ኮር ተወካዮችና የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ፣ አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ በቆይታቸው በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል የነበረውን ታሪካዊ ወዳጅነት ይበልጥ ማጠናከራቸውን ገልጸዋል።

በተለይም ከረጅም ዓመታት የወታደራዊ ሕይወታቸው ያመጡትን ከፍተኛ የዲስፕሊንና የቁርጠኝነት እሴት ለስኬታቸው መሠረት በማድረግ የሀገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም አስከብረዋል።

አምባሳደሩ ከኬንያ መንግሥት ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እና ከኤምባሲው ሠራተኞች ጋር ያሳለፉትን ስኬታማ የሥራ ጊዜ በማውሳት ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በዕለቱም ላበረከቱት አስተዋጽኦ ማሳያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የማስታወሻ ስጦታዎች ተበርክተውላቸዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1