የአንድ ክፍለ ዘመን ሕያው ታሪክ

- Advertisement -
Sidebar AD

ከፈረስ ጋሪ እስከ AI የተመለከቱ አባት!

#Ethiopia | ዓለም ከፈረስ ጋሪ ወደ ጠፈር መንኮራኩር፣ ከደብዳቤ ወደ አርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ ስትሸጋገር በአካል ተገኝተው የተከታተሉ ድንቅ የእድሜ ባለፀጋ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ጽፈዋል።

በፈረንጆቹ 1915 በአሜሪካ ሚሲሲፒ ግዛት የተወለዱት ሜጀር ጁዌል ማክዶናልድ በ110 ዓመታቸው በሕይወት ያሉ የአሜሪካ አንጋፋ የእድሜ ባለፀጋ መሆናቸው ተረጋገጠ።

እሳቸው ወደእዚህ ዓለም ሲመጡ ባለቀለም ቴሌቪዥን የግል ኮምፒውተሮች ቀርቶ ዛሬ እጃችን ላይ ያሉት ዘመናዊ ስማርት ፎኖች ፈጽመው አልታሰቡም ነበር።

የቴሌቪዥን መስፋፋትን የሰው ልጅ ወደ ጨረቃ ያደረገውን ጉዞ የኢንተርኔት እና የስማርትፎን አብዮትን ሙሉ በሙሉ በዓይናቸው ተመልክተዋል።

በወጣትነታቸው የ1930ውን አስከፊ የዓለም ታላቅ የኢኮኖሚ ድቀት ተሻግረዋል።

በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ እያሉ ደግሞ መላውን ዓለም ያናጋውን ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት በአካል አስተናግደዋል።

ከሁሉም በላይ የሚገርመው ነገር በ110 ዓመታቸው ሙሉ በጥሩ ጤንነት ላይ መገኘታቸው ብቻ ሳይሆን ዛሬም ድረስ የዕለት ተዕለት ቁርሳቸውን በገዛ እጃቸው የሚያዘጋጁ ንቁ እና በራሳቸው የሚተማመኑ መሆናቸው ነው።

በእነዚህ 110 ዓመታት ውስጥ በዓለማችን ላይ የተከሰቱትን ግዙፍ ታሪካዊና ቴክኖሎጂያዊ ለውጦች ላስተዋለ ሰው የሜጀር ጁዌል ማክዶናልድ የሕይወት ጉዞ እጅግ የሚያስደንቅና ተአምረኛ ያደርገዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesge
#American #mississippi
#GreatDepression
#Worldwarll #technology


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2