ለሚወዷቸው ንጽሑ ወርቅ የሚያሸልሙበት ቀን ደርሷል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የቅን ልቦች የበጎ አድራጎት ድርጅት በማህበራዊ ሚዲያ አወንታዊ ተፅዕኖ የፈጠሩ አካላትን የሚያስመሰግንበትን “የአሸናፊዎች አሸናፊ” የሽልማትና የእውቅና መርሃ-ግብር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አደረገ።

ድርጅቱ ባለፉት ስድስት ዓመታት የማህበራዊ ሚዲያን ለሀገር፣ ለሰላም፣ ለአንድነትና ለሀገራዊ እሴቶች ግንባታ በበጎ መንገድ ሲጠቀሙ የነበሩ አካላትን ሲሸልም የቆየ ሲሆን በዘንድሮው መርሃ-ግብርም በቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቴሌግራም የጎላ አስተዋፅኦ ያበረከቱ 33 ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለማስመስገን ዝግጅቱን አጠናቋል።

​በዚህ ታላቅ መርሃ-ግብር ለተወዳዳሪዎች የተዘጋጀው የወርቅ ሽልማት መጠን ቀደም ሲል ከተያዘው 100 ግራም ወደ 280 ግራም ንጹህ ወርቅ ከፍ ያለ ሲሆን አጠቃላይ የገንዘብ ግምቱም እስከ 15 ሚሊዮን ብር ይደርሳል።

ሽልማቱ በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ተከፍሎ የሚሰጥ ሲሆን በዓመቱ ምርጥ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ዘርፍ ለወጡ 6 ግንባር ቀደም አሸናፊዎች 180 ግራም ወርቅ ተዘጋጅቷል።

በሌላ በኩል በእውቀታቸውና በሙያቸው ለሀገርና ለትውልድ አሻራ ያኖሩ አርአያ ዜጎችን በሚያበራታታው ሁለተኛ ዘርፍ የመጀመሪያ ደረጃ ለሚያገኘው ተወዳዳሪ 100 ግራም ወርቅ፣ ለሁለተኛው 50 ግራም ወርቅ እንዲሁም ለሦስተኛው 30 ግራም ወርቅ ይሸለማሉ።

በተጨማሪም ለሌሎች በርካታ የደረጃ ሽልማቶችና ከ10 በላይ ለሚሆኑ አንጋፋ የሀገር ባለውለታዎች ልዩ የምስጋናና ዝግጅት ይኖረዋል።

​ይህንን ግዙፍ መርሃ-ግብር በቴክኖሎጂና በፋይናንስ ለማሳካት ሳንቲ ፔይ፣ ሰበዝ ቴክኖሎጂ እና አዳራሽ ዶትኮም በዋና አጋርነት ተሳትፈዋል።

የድምፅ መስጫ ዌብሳይትና አፕሊኬሽን አሁን ላይ በይፋ የተከፈተ ሲሆን ህዝቡ ድምፅ በሚሰጥበት ወቅት የመጀመሪያው ድምፅ ነፃ እንዲሆን ተደርጓል።

ዛሬ በተካሄደው የጋዜጣዊ መግለጫ መድረክ ላይ የቅንልቦች የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተስፋዬ ስንሻው፣ የሳንቲ ፔይ ተወካይ አቶ እርሻሎም እንድሪያስ እና የሰበዝ ቴክኖሎጂ ተወካይ አቶ ደረጀ ተገኝተው የመርሃ-ግብሩን ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

​በዕጩነት ከቀረቡት ታዋቂ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና የዲጂታል ሚዲያ አካላት መካከል ባርኮት፣ ዶክተር አብይ፣ ዩቲ ናስ፣ አዶናይ፣ ጌታቸው መለሰ፣ ብሩክ News፣ ሜላት ንጉሴ፣ ማስተር አብነት፣ ኮሜዲያን ያሲኖ፣ አውንታ በርሲሳ፣ አቲስ ነማ በጎ አድራጎት፣ ጉርሻ ፔጅ እና ጆን ዳንኤል ይገኙበታል።

የህዝብ ድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በይፋ መጀመሩን ተከተሎ “የአሸናፊዎች አሸናፊ” የሚለውን ታላቅ የክብር ዘውድ ማን ይጎናጸፋል የሚለው በጉጉት የሚጠበቅ ይሆናል።

📌ለጌጡ ተመስገን ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ ከታች ባለው ሊንክ ድምፅ ይስጡ

https://yekinlibochaward.org/nominees/getu-temesgen

📸 ከበደ መክብብ

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1