#Ethiopia | የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መዝጊያ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የዓድዋ ድል የመላው አፍሪካውያን የነጻነት ተምሳሌት መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ የአፍሪካ የነጻነትና የውሳኔ ማዕከል መሆኗን የጠቆሙት ኬንያታ፣ የኢትዮጵያ ባህላዊና ታሪካዊ ብዝኃነት ሀገሪቱን እንደ ማራኪ የሥዕል ቅብ የሚያስውብ ሀብት እንደሆነ አብራርተዋል።
በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ሲናገሩም “ማንኛውም ቤተሰብ ቢጣላም ቤቱ ግን አንድ ነው” በማለት የፖለቲካ ልዩነቶች በጦርነት ሊፈቱ እንደማይገባቸው አሳስበዋል።
ለኢትዮጵያ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ የሚገኘው ከራሱ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በመሆኑ ሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል።
አክለውም፤ ቀጣዩ የሰላም ጉዞ በጉባኤው ያልተገኙ አካላትን ያካተተ መሆን እንዳለበት ገልጸው፤ ኢትዮጵያና ኬንያ ላለፉት ዓመታት ያለ ምንም ግጭት ድንበራቸውን በሰላም በማካለል ያሳዩት ወንድማማችነት ለሌሎች አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል።
#ኢትዮጵያ #ሀገራዊምክክር #ኡሁሩኬንያታ #ሰላምለኢትዮጵያ #የአፍሪካአንድነት #EthiopiaNationalDialogue #UhuruKenyatta #AfricaUnite#ሀገራዊምክክር #EthiopiaNationalDialogue #UhuruKenyatta #AfricaUnite #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.