#Ethiopia | ከ150 በላይ ሰዎች የተሳተፉበት “አበጋር” ፊልም ማክሰኞ ነሀሴ 19 ለእይታ እንደሚበቃ ሰምተናል።
“አበጋር” ፊልም ማክሰኞ ነሀሴ 19 በፍላሚንጎ በሚገኘው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትር አዳራሽ ለእይታ እንደሚበቃ የፊልሙ ፕሮዲውሰር ንጉሴ ሙሉጌታ በመግለጫቸው አስታውቀዋል::
“አበጋር” በተባለው ባህላዊና ትውፊታዊ የእርቅና የግጭት አፈታት ሥርዓት ላይ የሚያተኩር ነው ብለዋል።
ይህም በሰሜንና ደቡብ ወሎ አካባቢዎች ያሉትን ባህላዊ የህግና የእርቅ ሂደቶች የሚያሳይ ነው።
የአበጋር ፊልም ደራሲና ዳሬክተር ጌታቸው ፋንታሁን አበጋር የሽምግልና ሥነ ሥርዓት በአብዛኛው የወሎ አካባቢ ማኅበረሰቡ የሚጠቀምበት የዳኝነት እና የእርቅ ሥነ ሥርዓት ነው ብለዋል።
አበጋር የሚለው ቃልም አስታራቂ የሚል ፍቺ እንዳለው ዳሬክተሩ ተናግሯል።
አበጋር የተጣላን የሚያስታርቅ ክፉ እንዳይሠራ በሀገር ሽማግሌዎች ፊት ተው የሚባልበት እና መጥፎ ነገሩን ዱአ ወይም ጸሎት አድርገው ወደ ፈጣሪ በመለመን በተጣሉት ሰዎች መካከል ጥላቻን የሚያርቁበት ሥርዓት መሆኑን ነግረውናል።
የአበጋር ፊልም ፕሮዲውሰር ንጉሱ ሙሉጌታ እንደገለፁት ቀረጻው በደሴ አካባቢ ለ4 ወራት ያህል የተከናወነ ሲሆን ኤዲቲንግን ጨምሮ አጠቃላይ ስራው ከ2 ዓመታት በላይ መውሰዱ ገልጸዋል።
ፊልሙ ሠርቶ ለማጠናቀቅ ከ5.6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገ የፊልሙ ፕሮዲውሰር ንጉሴ ተናግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.