#Ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን የባንኩ ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ለመሾም ያቀረበውን ጥያቄ መስፈርቶችን አላሟላም በሚል ውድቅ እንዳደረገው ከ ዘ ሪፖርተር ማጋዚን ሰምተናል።
ብሔራዊ ባንክ ለግሎባል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ እንደገለጸው፣ የቀረቡት ሰነዶች ሲገመገሙ አቶ ሳህለሚካኤል በባንኩ መመሪያ ቁጥር SBB/89/2024 አንቀጽ 5.1.3 (ለ) ላይ የተደነገገውን ዝቅተኛ የሥራ ልምድ መስፈርት አያሟሉም።
በዚህም ምክንያት ግሎባል ባንክ በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 1360/2017 የተመለከቱትን ህጋዊ የብቃት መስፈርቶች የሚያሟላ ሌላ አማራጭ ዕጩ መርጦ እንዲያቀርብ ታዟል።
የግሎባል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአቶ ሳህለሚካኤልን ሹመት በሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም ያጸደቀ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክን ፈቃድ ለማግኘት በሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ማመልከቻ ማስገባቱ ይታወሳል።
የባንኩ የማርኬቲንግ እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ፍቃዱ የብሔራዊ ባንክን ውሳኔ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ባንኩ በቀጣይ አዲስ ዕጩ አቅርቦ የሚያስጸድቅ ይሆናል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.