ቱርክ ኢንተርፖል አይኑን የእስራዔሉ መሪ ላይ እንዲያደርግ ጠየቀች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ቱርክ ለጋዛ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ይጓዝ በነበረው የፍሎቲላ የባህር ስብስብ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ምክንያት በኢስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና በአፌክ ሞስኮቪች ላይ ዓለም አቀፍ የኢንተርፖል (Red Notice) እንዲወጣ መጠየቋን የሀገሪቱ የፍትህ ሚኒስትር አኪን ጉርሌክ አስታወቁ።

በኢስታንቡል 11ኛ ከፍተኛ የወንጀል ችሎት በመታየት ላይ ባለው በዚህ የክስ መዝገብ 35 ተከሳሾች የተካተቱ ሲሆን በሐምሌ ወር የወጣውን የእስር ትእዛዝ ተከትሎ የተጀመረው ይህ ሂደት በዓለም አቀፍ የውሃ አካል ላይ በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመውን የጦር መሳሪያ ጥቃት ያካተተ ነው።

ተከሳሾቹ የዘር ማጥፋት፣ በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች፣ ማሰቃየት፣ ሰዎችን ያለሕግ አግባብ ማሰር፣ ዘረፋ እና የትራንስፖርት መርከቦችን ማገት በሚሉ ከባድ ወንጀሎች የተከሰሱ ሲሆን የፍትህ ሚኒስትሩ አኪን ጉርሌክ በጋዛ የተፈጸሙ ወንጀሎች ያለጠያቂ እንዲቀሩ ወይም ተጠያቂዎች ከተጠያቂነት ነፃ በሆነ ከለላ እንዲሸሸጉ እንደማይፈቅዱ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን መሪነት ቱርክ ከፍልስጤም ህዝብ ጎን በጽናት እንደምትቆም እና በወንጀል የተጠረጠሩ አካላትን ለህግ ለማቅረብ ሁሉንም ህጋዊ መንገዶች በቁርጠኝነት እንደምትጠቀም አስታውቀዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: