የኔቶ አባላት ሆርሙዝ ወሽመጥን በተመለከተ ያሉ አማራጮች ላይ መወያየታቸው ተዘገበ

- Advertisement -
Sidebar AD

በሆርሙዝ ወሽመጥ በነጻነት መንቀሳቀስ የሚቻልበትን መንገድ ለማሳለጥ ያለመ እና በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ከፍተኛ ኮማንደር የተመራ ውይይት መደረጉን ሮይተርስ ዘገበ።
ሮይተርስ የዜና ወኪል የከፍተኛ ኮማንደሩን ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ያለፈው ረቡዕ በአውሮፓ አጋር አገራት ዋና መሥሪያ ቤት በከፍተኛ የመከላከያ አመራሮች ደረጃ ውይይት ተደርጓል።

አጋር አገራቱ በሆርሙዝ ወሽመጥ በነጻነት ለመጓጓዝ እንዲቻል ምን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚችሉ በውይይቱ መነሳቱ ተገልጿል።
የአጋር አገራቱ ከፍተኛ ኮማንደር ቃል አቀባይ የሆኑት የአሜሪካ አየር ኃይል መሪ አሌክሱስ ግራንክዊች ትናንት አርብ “ይሄ የኔቶ ተልዕኮ እንዳልሆነ ግልጽ መሆን አለበት” ብለዋል።
“ኔቶ አጋሮችን አንድ ላይ የማምጣት እና አቅማቸውን የመረዳት ልዩ ብቃቱን ተጠቅሞ ያመቻቸው ነው” ሲሉም አክለዋል።
የኔቶ አገራት በኢራን ጦርነት በቀጥታ ላለመሳተፍ እየሞከሩ ሲሆን፤ የሆርሙዝ ወሽመጥ የሚከፈትበትን አማራጭ መንገድ መፈለግ ግን ቀጥለዋል።
ግጭቱ ከረገበ በኋላ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞን ለማረጋገጥ የአገራት ትብብር እንዲኖር ለማስቻል ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም ጥረት አድርገዋል።

ዘላቂ ስምምነት ላይ ለመድረስ ግን የግድ የኢራን ፈቃደኛነት ያስፈልጋል።

BBC



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1