#Fastmereja I በዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በአራዳ ጊዮርጊስ (ፓራዳይዝ) ስፔሻላይዝድ ሕክምና ማዕከል አጋርነት ለሕፃናት ነጻ የቶንሲል እና የአዴኖይድ (የአፍንጫ መተንፈሻ) የቀዶ ሕክምና ዘመቻ ተካሄደ።
ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው በዚህ የበጎ አድራጎት ዘመቻ፣ በመንግሥት ሆስፒታሉ በሕክምና ወረፋ ላይከነበሩ ከ700 በላይ ታካሚዎች መካከል ቅድሚያ የተሰጣቸውን እስከ 60 የሚደርሱ አጣዳፊ የጤና ችግርያለባቸውን ሕፃናት ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።
ሕመሙ በሕፃናት ላይ የመታፈን፣ የማንኮራፋትና የእንቅልፍ ማጣት ችግርየሚያስከትል ሲሆን፣ በጊዜ ካልታከመ ለልብ ቫልቭጉዳትና ለልብ ድካም ሊዳርግ ይችላል ሲሉ የአራዳ ጊዮርጊስ ማዕከል የአንገት በላይ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ኃይለማርያም ታፈሰ ገልፀዋል።
በመሆኑም የቀዶ ሕክምናው ሕፃናቱ የክረምት እረፍታቸውን ተጠቅመው በማገገም ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ ነፃ ህክምና በግል ሕክምና ተቋማት ለአንድ ታካሚ እስከ 70,000 ብር ሊያስወጣ የሚችለውን ይህን ሕክምና በነጻ በመስጠት፣ በአጠቃላይ ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይየሚገመት የሕክምና ወጪ መሸፈን ተችሏል።
ዘመቻው የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነትን የሚያጠናክርና በመንግሥት ሆስፒታሎች ላይ ያለውን የረጅም ጊዜ ወረፋ ጫና የሚቀንስ መሆኑ ተገልጿል።
የነጻ ቀዶ ሕክምና መርሃ ግብሩ የመጀመሪያ ዙር በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን፣ ሁለተኛው ዙር ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ እንደሚካሄድ ታውቋል።
አራዳ ጊዮርጊስ ስፔሻላይዝድ የህክምና ማዕከል በቅርቡ በተቋሙ ባደራጀው የአንገት በላይ የህክምና ማእከል ዘመናዊ የሆነውን የካርቦንዳይድ ኦክሳይድ ሌዘር ማሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀዶ ጥገና ወቅት የሚከሰትን ከፍተኛ የደም መፍሰስን የሚቀንስና ከቀዶ ጥገና በዃላ የሚፈጠር እብጠትና ህመምን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ መሆኑ ተገልጿል።
📷ከበደ መክብብ



Source: FastMereja








No comments yet.