የትራምፕ ቪዛ እገዳ በፍርድ ቤት ተሻረየኒውዮርክ የፌደራል ፍርድ ቤት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ75 ሀገራት በ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የትራምፕ ቪዛ እገዳ በፍርድ ቤት ተሻረ
የኒውዮርክ የፌደራል ፍርድ ቤት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ75 ሀገራት በሚመጡ ዜጎች ላይ ጥሎት የነበረውን የኢሚግሬሽን ቪዛ እገዳ ውድቅ አደረገ።
​የፍርድ ቤቱ ዳኛ ጄኔት ቫርጋስ በሰጡት ውሳኔ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያሳለፈው ይህ እገዳ “በግልጽ ህገ-ወጥ” እና ከሚኒስቴሩ ህጋዊ ስልጣን ውጭ ነው ብለዋል።
ውሳኔው በዜግነት ላይ የተመሰረተ መድልዎ በመሆኑ ከሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ህግ ጋር እንደሚጋጭም ገልጸዋል።
​እገዳው ከአፍሪካ፣ ከላቲን አሜሪካ፣ ከእስያ እና ከአውሮፓ የመጡ የቪዛ አመልካቾችን የጎዳ ሲሆን፣ የትራምፕ አስተዳደር አመልካቾቹ “በመንግስት ላይ ጥገኛ የመሆን ስጋት አለባቸው” የሚል ምክንያት አቅርቦ ነበር።
​ክሱን የመሰረቱት የኢሚግሬሽን መብት ተሟጋች ድርጅቶች በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መደሰታቸውን ሲገልጹ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: