ዮሚፍ ቀጀልቻ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረ​ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በአርጀንቲና የተካሄደውን የቦነስ አ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ዮሚፍ ቀጀልቻ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረ
​ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በአርጀንቲና የተካሄደውን የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን ውድድር 56 ደቂቃ ከ51 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ዳግም አሻሽሏል።
​ዮሚፍ ኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ በሊዝበን ያስመዘገበውን የ57 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ የቀድሞ ክብረ ወሰን በ29 ሰከንዶች አሻሽሏል።j
ዮሚፍ እ.አ.አ. በ2024 ቫሌንሲያ ላይ 57 ደቂቃ ከ30 ሰኮንድ በመግባት ክብረ ወሰኑን ይዞ እንደነበር ይታወሳል። አትሌቱ በዓለም የግማሽ ማራቶን ንግስናውን በድጋሚ አረጋግጧል።
​በተመሳሳይ በሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፎይተን ተስፋይ ርቀቱን በ1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ57 ሰኮንድ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆናለች።
የዮሚፍ አዲሱ የዓለም ክብረ ወሰን የዓለም አትሌቲክስን ይፋዊ ማረጋገጫ የሚጠብቅ ይሆናል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: