#Ethiopia | ኢትዮጵያዊው የዩቲዩብ ይዘት ፈጣሪ አቤል ብርሃኑ በናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ በተካሄደው የፓን-አፍሪካ ሽልማት ላይ የዓመቱ ከፍተኛ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመባል በመመረጥ የሀገሩን ስም በማስጠራት ትልቅ ድል አስመዝግቧል።
ዓለምን በዩቲዩብ ገፁ አማካኝነት የማስተዋወቅ ህልሙን ሰንቆ የተነሳው አቤል እስካሁን ባደረገው ጉዞ ወደ ዘጠና ሀገራት መጓዝ የቻለ ሲሆን ይህ የተቀናጀው ውጤት የሁሉም አበረታች ስኬት መሆኑን ተናግሯል።
ለዚህ የላቀ እውቅና በመብቃቱ ሁልጊዜ ከጎኑ ሆነው ለደገፉት ባለቤቱ፣ ለቤተሰቡ፣ አብረውት ለሚሰሩ የቡድን አባላት እንዲሁም ሁልጊዜ የማበረታቻ መልዕክት ለሚልኩለት ተከታዮቹ የከበረ ምስጋናውን አቅርቧል።
የጉዞ ፕሮግራሙ በበለጠ ጥራትና ስፋት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
የአቤል ጉዞ
ይቀጥላል …
#abelbirhanu #travelvlog #palca2026 #ethiopianinfluencer #youtubeethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.