#FastMereja I ግሎባል ጀነራል ኮንስትራክሽን ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በሐዋሳ ሐይሌ ሪዞርት ባካሄደው መድረክ የ2018 የበጀት ዓመት የሥራ እንቅስቃሴውን ከድርጅቱ ሰራተኞች ጋር በመሆን ገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ ላይ በ2017 በጀት ዓመት ግንባታቸው ተጀምረው ተጠናቀው የተረከቡ፣ እንዲሁም በ2018 በጀት ዓመት ተጀምረው በጥሩ አፈጻጸም ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የደረሱበት ደረጃ እና የቀጣይ የሥራ ዕቅዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ከድር ሐሰን፤ የድርጅቱ ትልቁ መሣሪያና የሥኬቱ መሠረት ሠራተኞቹ መሆናቸውን በመግለጽ፣ እያንዳንዱ ሠራተኛ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል። አክለውም በበጀት ዓመቱ የላቀ የሥራ አፈጻጸም ላሳዩ የድርጅቱ ሰራተኞች እውቅና ሽልማት ሰጥቷል።
ግሎባል ጀነራል ኮንስትራክሽን፤ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ፣ በኦሮሚያ ክልል ከተሞች እንዲሁም በፌዴራል ተቋማት የተለያዩ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን በመገንባትና በማስረከብ ላይ ይገኛል።



Source: FastMereja









No comments yet.