ሴዶ ማርሻል እስከ 1 ዓመት እስራት ሊቀጣ ይችላል» — ጠበቃ ሰብለ አሰፋ::
በETFC 2 Cage ውድድር ውዝግብ ዙሪያ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጡ
አዲስ አበባ — በETFC 2 Cage ውድድር ዝግጅት ወቅት ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል “በተቃዋሚዬ ጆኒ ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል” በሚል ምክንያት ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን አስመልክቶ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠበቃ ሰብለ አሰፋ በቪዲዮ በሰጡት መግለጫ፣ ሴዶ ያቀረበው “በእንቁላል መተት ተሰርቶብኛል” የሚለው አቤቱታ በህግ ፊት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ካልቀረበበት በስተቀር በጆኒ ላይ የተፈጸመ የሐሰት ስም ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ገልጸዋል።
እንደ ጠበቃ ሰብለ ገለጻ፣ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 613 መሠረት፣ አንድ ሰው ያለበቂ ማስረጃ በሌላው ሰው ላይ የሐሰት ክስና ውንጀላ በማቅረብ መልካም ስሙንና ክብሩን ካደፈረሰ ወይም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመኔታ እንዲያጣ ካደረገ፣ በተጎጂው አቤቱታ አቅራቢነት እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ሊቀጣ ይችላል።
በተጨማሪም ውድድሩ መሰረዙ ከተረጋገጠ ወይም የተወደዱ ተወዳዳሪዎች ባለመሰለፋቸው ምክንያት ቅሬታ ያላቸው የትኬት ገዢዎችና ተመልካቾች የውድድሩን አዘጋጆች ካሳ የመጠየቅ ሙሉ ሕጋዊ መብት እንዳላቸው ጠበቃ ሰብለ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የውድድሩ አዘጋጆች (ETFC) ሴዶ ማርሻል በገባው ውል መሠረት ባለመወዳደሩ ምክንያት ለደረሰባቸው የወጪና የገቢ ኪሳራ እንዲሁም ለተመልካቾች ለሚከፍሉት ካሳ በፍትሐብሔር ሕግ መሠረት ከሴዶ ላይ የጉዳት ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ገልጸዋል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.