በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ2 ሺህ 400 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱበሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ2 ሺህ 400 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 494 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
በሳምንቱ ውስጥ በተደረጉ 12 ዙር በረራዎች ወደ ሀገር ከተመለሱት ዜጎች መካከል 2 ሺህ 312 ወንዶች፣ 163 ሴቶች እና 19 ጨቅላ ሕፃናት የሚገኙበት ሲሆን፤ 189ኙ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ዘመቻ ወዲህ እስካሁን ከ96 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።
ሚኒስቴሩ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ከመከላከል ጎን ለጎን ለተመላሾች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማቀላቀል ሥራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: