በውሻ እንግልት 475 ዓመት እስራት የተፈረደበት ግለሰብ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአሜሪካ ጆርጂያ ግዛት የሚገኝ አንድ የአማዞን እቃ አመላላሽ ግለሰብ የተመለከተውን አጠራጣሪ ነገር ችላ ሳይል ለህግ አስከባሪዎች የሰጠው ጥቆማ በታሪክ ከፍተኛውን የፍርድ ውሳኔ እንዲተላለፍ ምክንያት ሆኗል።

እቃ አመላላሹ በስራ አጋጣሚ ወደ ግለሰቡ ቅጥር ግቢ ሲገባ በዛፎች እና በትላልቅ ብረቶች በከባድ ሰንሰለቶች የታሰሩ ውሾችን ተመለከተ።

ሁኔታው የከፋ የእንስሳት እንግልት መሆኑን የተረዳው ይህ ግለሰብ ወዲያውኑ ለፖሊስ አካላት ጥቆማ ሰጠ።

መርማሪ ፖሊሶች በደረሳቸው ጥቆማ መሠረት በቦታው ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ከ103 በላይ ውሾች በአሰቃቂ ሁኔታ ታስረው ማግኘታቸውን ገለፁ።

በቦታው የተገኙት ማስረጃዎች ግለሰቡ ህገ-ወጥ እና የተደራጀ የውሻ ማጎርያ ያካሂድ እንደነበር መርማሪዎች አረጋግጠዋል።

የዚህ አሰቃቂ ድርጊት ፈጻሚ የሆነው ቪንሰንት ሌማርክ በርል የተባለው ግለሰብ በመጨረሻም ፍርድ ተሰጥቶታል።

ተከሳሹ የቀረቡበትን 103 የጉዳት እና የእንስሳት እንግልት ክሶች ማስተባበል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ተብሏል።

በዚህም ግለሰቡ በእንስሳት ላይ የፈጸመው ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን የገለጸው ፍ/ቤቱ በ475 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ይህ የፍርድ ውሳኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ በእንስሳት መብት እና እንግልት ዙሪያ የተላለፈ ከፍተኛው እና ታሪካዊው ውሳኔ እንደሆነ ተገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#America #Georgia
#Amazondelivery
#Dozensdogs #prison
#convicted
#VincentLemarkBurrell


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1