አዲስ አበባ : በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አደጋው የደረሰው ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡

የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል 5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ

​#addisababa #trafficaccident #ethiopiannews #bole #ethiopiapolice #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1