🙏
ቤተክርስቲያናችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ በማለት ክብሯን ትገልጻለች።
ኦርቶዶክሳዊያን ከሕጻንነታችን ጀምረን የእመቤታችንን ምስጋና እንማራለን፣ ሁልጊዜም በአባታችን ሆይ ጸሎት ጀምረን በመልኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ብለን ድንግል ማርያምን እናመሰግናታለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ የምትመሰገን ናት። እርሷ ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት በሰው ህሊና የሚለካ ምሳሌ ማጣታቸውን ብዙ ቅዱሳን ተናግረዋል። የብህንሳው ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ፣ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምና ኢትዮጵያዊው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ክብሯን ገናንነቷን በስፋት ተናግረዋል፣ አመስግነዋታል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት።
ጌታችን አምላካችን ኢየሱ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ፤ በእርሷም የመለኮትና የስጋ ፍጹም ተዋህዶ ተፈጸመ፡፡ የማይወሰነውን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ ወሰነችው፡፡ ከዓለም በፊት ከአብ ያለእናት እንደተወለደ፣ ከእርሷ ደግሞ ድህረ ዓለም ያለ አባት ተወለደ፡፡ አምላክ እኛን ለማዳን ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ ስንል በተዋህዶ ነውና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አማላክ ትባላለች፡፡ እመቤታችን በሀሳብም በሥጋም ዘላለማዊት ድንግል ናት። በሀሳቧ በህሊናዋ ከአምላክ ህግና ሀሳብ በስተቀር ስጋዊ ሀሳብ ፈጽሞ ኖሮ አይውቅምና ከሰው ወገን ተለይታ የህሊና ድንግልና አላት፡፡
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች መሆኗን በመመስከር ይህን የህሊና ድንግልና ያስረዳናል። መልአኩም ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ ሲያበስራት “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል” ብላ መናገሯ “ስለ ወንድ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም” ማለቷ ነውና የህሊና ወይም የሀሳብ ድንግልናዋን ያስረዳናል። ከመፅነሷ በፊት፤ በፀነሰች ጊዜ፤ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደችም ጊዜ፤ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡ ገዳማውያን ይህን ክብሯንና አማላጅነቷን አምነው ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ የበረከቱ ተካፋይ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000766349227
ወይም
አቢሲንያ ባንክ
262281132
የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921
Source: FastMereja









No comments yet.