#Ethiopia | በማላዊ በትዳር አጋሮቻቸው ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ አድሮባቸው የዲኤንኤ ምርመራ ያደረጉ ወንዶችን አስመልክቶ የወጣው መረጃ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
በሀገሪቱ የዘር ፍሬ ምርመራ ካደረጉት ጥርጣሬ ያደረባቸው ወንዶች መካከል 80 በመቶ ያህሉ የልጆቹ እውነተኛ አባቶች አለመሆናቸው ተገልጿል።
ይህ ይፋ የሆነው አኃዝ በብዙ ቤተሰቦች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትንና ክርክርን ጭሯል።
ነገር ግን ይህ ስታቲስቲክስ የሚያመለክተው ቀድሞውኑ ጥርጣሬ አድሮባቸው ወደ ምርመራ ተቋማት የሄዱትን ወንዶች ብቻ ነው።
በመሆኑም መረጃው በጠቅላላው በማላዊ የሚገኙ አባቶችን ሁኔታ የሚያንጸባርቅ እንዳልሆነና የሁሉም አባቶች እውነታ ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት ባለሙያዎች ያብራራሉ።
#malawi #dna #dnatest #africa #africanews #family #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen








No comments yet.