#Ethiopia | በፓሪስ ከተማ ለሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የኢ-ስፖርትስ ዓለም ዋንጫ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት የሳውዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን እና የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።
ከኮምፒዩተር ጨዋታዎች እስከ ቼዝ ያሉ የተለያዩ የዲጂታል ስፖርት ዘርፎችን ያካተተው ይህ ታላቅ ውድድር ከሳውዲ አረቢያ ውጭ ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የመጀመሪያዎቹ ሁለት የኢ-ስፖርትስ ዓለም ዋንጫ ውድድሮች በሳውዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በከፍተኛ ድምቀት የተስተናገዱ ቢሆንም በቀጣናው በተከሰተው የጂኦፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ለ2026ቱ ውድድር አዲስ አዘጋጅ ከተማ መምረጥ አስፈላጊ ሆኖ ነበር።
ባለፈው ግንቦት ወር አዘጋጅነቱ የተሰጣት ፓሪስ ውድድሩን ከሪያድ በተሳካ ሁኔታ በመረከብ አዘጋጅነቷን በብቃት ተወጥታለች።
ከሐምሌ 3 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው በዚህ ውድድር ከ100 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ2,000 በላይ ተወዳዳሪዎች እና 200 ክለቦች ተሳትፈዋል።
በእሁዱ የእስክሪን ላይ ፍልሚያ የቻይናው “ኦል ጌመርስ” ቡድን የሁለት ጊዜ አሸናፊውን የሳውዲ አረቢያውን “ቲም ፋልኮንስ” በመረታት የቪዲዮ ጌሚንግ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ማክሮን ከአሸናፊዎች ጋር ተወያይተው ዋንጫዎችን ያበረከቱ ሲሆን ውድድሩ በ160 ሀገራት በቀጥታ ስርጭት ለተመልካች ደርሷል።
የዓለማችን የምንግዜም ምርጥ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዝግጅቱ ላይ የተገኘ ሲሆን ከልዑሉ ጋር ሰላምታ ተቀያይረዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.