9ኛው ዓመታዊ የጳጉሜ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:- «ጳጉሜ፤ የአፍሪካ ወርቃማ ወር» በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 9ኛው ዓመታዊ የ«ጳጉሜ አብ ፌስቲቫል» ከጳጉሜ 1 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁን አዘጋጆቹ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ።

በጳጉሜ አብ ፌስቲቫል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አዘጋጅነት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ፌስቲቫል፤ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህላዊ እሴቶች፣ የኪነ-ጥበብ ሀብቶችና የኢንቨስትመንት አማራጮች ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ጎብኚዎች ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዲፕሎማቲክ ኮሚኒቲ አባላት፣ የ12ቱ ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የባህል ቡድኖች እንዲሁም ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ በመግለጫዉ ተገልጿል።

በተጨማሪም ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን ልዩ የ13ኛ ወር ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና ጳጉሜ በUNESCO ደረጃ እንድትመዘገብ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ አዘጋጆቹ አብራርተዋል።

ፌስቲቫሉ በአምስቱ ቀናት በተለያዩ ጭብጦች ተከፋፍለው የሚካሄዱ ሲሆን፣ ዋና ዋና መርሃ-ግብሮቹም፡-

ጳጉሜ 1 (ለሰላምና ለፍቅር): የፖሊስ ማርሽና የፈረስ ጉግስ ትርኢት፣ የከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ንግግር እና ስለ ሰላምና እርቅ የሚያተኩርየፓናል ውይይት፣

ጳጉሜ 2 (ለባህልና ለአፍሪካ አንድነት): የሁሉም ክልሎች ተወካዮች የሚሳተፉበት ባህላዊ የፋሽን ሾው እና የባህላዊ ምግቦችና መጠጦች ቅምሻ፣

ጳጉሜ 3 (ጳጉሜ ለልጆች): «ታላቁ ሩጫ በዝናብ»፣ የህፃናት ባህላዊ ጨዋታዎችና የመዝናኛ ፕሮግራሞች፣

ጳጉሜ 4 (እንነግድ በጳጉሜ): የአፍሪካውያንን የጋራ ገበያ የሚያጎለብት የንግድ ትስስር (B2B) እና የንግድ ፓናል ውይይት፣

ጳጉሜ 5 (የተፈጥሮ ውበታችን ለቱሪዝም መስህብ): የጳጉሜ ቆንጆ ውድድር፣ የቱሪዝም ውይይት እና የስፖንሰሮች የእውቅና ፕሮግራም ይከናወናሉ።

የፌስቲቫሉ መደበኛ የመግቢያ ዋጋ 500 ብር ሲሆን፣ በመጨረሻው ቀን ለሚካሄደው ታላቅ የሙዚቃ ድግስ የመግቢያ ክፍያው 1,500 ብር መሆኑ ተጠቅሷል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: