የሴዶ ማርሻል ”መልዕክት” እስከ አንድ ዓመት በእስር ሊያስቀጣው ይችላል ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የኢትዮጵያ ፋይቲንግ ቻምፒዮንሺፕ (ETFC) ውድድር ጥቂት ቀናት ብቻ በሜቀሩበት ወቅት ተወዳዳሪው ሴዶ “ድግምት ተሰርቶብኛል” በሚል ከውድድሩ መውጣቱን ማስታወቁ በማህበራዊ ሚዲያ እና በስፖርቱ አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ ፈጥሯል።

​ሴዶ ከውድድሩ አራት ቀናት ቀደም ብሎ ባስተላለፈው መልዕክት ከተጋጣሚው ጆኒ ጋር ለሚያደርገው ፍልሚያ እንደማይቀርብ ይፋ አድርጓል።

ተወዳዳሪው በእንቁላል ድግምትና ስህር እንደተሰራበት በመግለጽ ከተለየ የውጭ አገር ተደባዳቢ ጋር ካልሆነ በስተቀር ከተጠቀሰው ተጋጣሚው ጋር ወደ ሪንግ እንደማይገባና የውድድሩን ቲሸርት አውልቆ በመመለስ አቋሙን አስታውቋል።

​ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡ የሕግ ባለሙያዋ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ እንደሚያስረዱት ሴዶ ያቀረበውን የድግምት ክስ በህግ ፊት የሚያስረዳ አደራጅ ማስረጃ ካላቀረበ፣ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ መሰረት በሰው ስም እና ክብር ላይ የሚፈጸም የሀሰት ሀሜትና ስም ማጥፋት ወንጀል ተደርጎ ሊወሰድበት ይችላል።

ይህም አሰራር የተጋጣሚውን መልካም ስም ያጎደለ በመሆኑ እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ሊያስቀጣው የሚችልበት ህጋዊ እድል እንዳለ ይጠቁማል።

​በሌላ በኩል ለውድድሩ ቲኬት የቆረጡ ተመልካቾች እና የውድድሩ ስፖንሰሮች መብት በህግ የተጠበቀ በመሆኑ የውድድሩ አዘጋጆች (ETFC) አማራጭ ውድድር የማቅረብ ወይም የገንዘብ ተመላሽ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

በተጨማሪም የውድድሩ አዘጋጆች ሴዶ በገባው ውል መሰረት ውድድሩን በማቋረጡ ምክንያት የደረሰባቸውን የገንዘብና የመድረክ ኪሳራ በፍትሐብሔር ክስ የመጠየቅ ሙሉ ህጋዊ መብት እንዳላቸው ተገልጿል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: