በፊትበኦሮሚያ ክልል የደገም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በታጣቂዎች ተገደሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ትናንት ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በደረሰ የጥቃት አደጋ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ደሴ መገደላቸው ተገለጸ።

ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳው አኖ ቀሬ ቀበሌ ውስጥ ሲሆን፣ በተመሳሳይ አጋጣሚ የቀበሌው ሊቀ መንበር አቶ አስፋወሰን ኃይሌን ጨምሮ ሌሎች ሰዎችም አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

በዕለቱ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር የጠቀሱት የዞኑ የጸጥታ መዋቅር ምንጮች፣ ለጥቃቱ በክልሉ የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ተጠያቂ አድርገዋል።

ታጣቂ ቡድኑም ሆነ የዞኑ እና የክልሉ አስተዳደር አካላት ስለሁኔታው እስካሁን የሰጡት ይፋዊ መግለጫ የለም።

በሰሜን ሸዋ ዞን በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ጥቃት ሲፈጸም የመጀመሪያው አለመሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ቀደም ሲልም የሱሉልታ እና የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ በርካታ የዞን ኃላፊዎች ተመሳሳይ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ (BBC Afaan Oromoo)



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1