3ኛው የአፍሪካ ስታር ዋይድ አዋርድ በመስከረም ወር ይካሄዳል!“ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ፤ መመሰጋገን ባሕላችን እናድርግ” …

- Advertisement -
Sidebar AD
3ኛው የአፍሪካ ስታር ዋይድ አዋርድ በመስከረም ወር ይካሄዳል!
“ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ፤ መመሰጋገን ባሕላችን እናድርግ” በሚል መሪ ቃል የሚከናወነው 3ኛው ዙር የአፍሪካ ስታርዋይድ አዋርድ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት በመጪው መስከረም ወር እንደሚካሄድ አዘጋጁ ከለር ፉል ኢቨንት ኦርጋናይዘር በዛሬዉ እለት በአምባሳደር ሆቴል በሰጠዉ መግለጫ አስታዉቋል።
በዝግጅቱ ላይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ከአፍሪካ ህብረት (Aሀ) የተወጣጡ ተወካዮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የውጭ ሀገራት እንግዶች እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንደሚታደሙ ተጠቅሷል።
የዘንድሮው ዝግጅት ከአምናው በበለጠ አድማሱን በማስፋት አህጉራዊ ተደራሽነት ያለው እንዲሆን መደረጉ ተገልፆ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ምሁራንና ባለሙያዎች በዳኝነትና በኮሚቴነት መካተታቸዉም ነዉ የተገለፀዉ።
ሽልማቱ በተለያዩ 11 ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን የአመራር አባልና ኢንቨስትመንት ዘርፍ፣ የኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፍ፣አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ባንክ፣ አቪየሽንና ቱሪዝም፣ሴትና ወጣት ስራ ፈጣሪዎች፣ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንደሆኑ ተገልጿል።
የአዋርዱ ዋነኛ አላማ በዘርፉ የለፉና የደከሙ ግለሰቦችንና ተቋማትን ፈልፍሎ በማዉጣት የሃገር ባለዉለታ ስለመሆናቸዉና በትዉልዱ ዘንድ ሊመሰገኑ ሊዘከሩ እንደሚገባና ትዉልዱም ከመልካም ሥራቸዉና ከዘወትር ትጋታቸዉ ልምድ እንዲቀስም እድሉን ለማመቻቸት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት አቅም ለውጭ ሀገር አልሚዎች ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል የሚፈጥር በመሆኑ፣ አሸናፊዎችን በትክክል ለመለየት ከሙያተኞች ግምገማ በተጨማሪ ህዝቡ በድረገፅ አማካኝነት በስልክ፣ በአሜይል፣ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ጥቆማዎችን መስጠቱን እንዲቀጥል አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።
የአፍሪካ ስታርዋይድ አዋርድ ለሕዝብ እና ለአገር በጎ ነገር ያበረከቱ ግለሰቦችና ስኬታማ የኢኮኖሚ ጃግኖች፣ በትጋት በቅንነት እና በሀገር ፍቅር መስራት ተምሳሌት የሆኑ አመራሮች፣ ዉስጥ በመሳተፍ በሙያቸዉ አንቱ ለተባሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅና የሚያበረክት ነዉ።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2