በልዩ የድምፅ አወጣጡ እና በመድረክ ላይ ባለው ማራኪ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ የራሱን አሻራ ማሳረፍ የቻ

- Advertisement -
Sidebar AD

በልዩ የድምፅ አወጣጡ እና በመድረክ ላይ ባለው ማራኪ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ የራሱን አሻራ ማሳረፍ የቻለው ድምፃዊ ኃይሉ አመርጋ፣ የመድረክ ስራዎች ለዕይታ በቁ ።

በሮክ እና በሀገርኛ ሙዚቃ ውህድ አዲስ አብዮት ከፈጠረው “ጃኖ ባንድ” ጋር ለዓመታት በርካታ ተወዳጅ ሥራዎችን ለሙዚቃ አፍቃሪዎች ሲያቀርብ የቆየው ኃይሉ፣ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የመጀመሪያውን የበኩር የብቻ (Solo) አልበም ለሕዝብ ጆሮ ማድረሱ ይታወሳል። ይህንኑ ስኬታማ አልበም መለቀቅ ተከትሎ፣ ድምፃዊው በተለያዩ መድረኮች ላይ ተገኝቶ ሥራዎቹን የማቅረብ ሰፊ ዕድል አግኝቷል።

ከእነዚህ መድረኮች መካከል በተለየ ሁኔታ የሚጠቀሰው፣ በሀገር ውስጥ የሙዚቃ መድረኮች ላይ ትልቅ ስፍራ ከሚሰጠው እና ተወዳጅነትን ካተረፈው ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ሴንተር ያቀረቡት ግዙፍ የሙዚቃ ኮንሰርት ነው። የሁለቱ አንጋፋ እና ወጣት ከዋክብት ጥምረት ታዳሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ያዝናናበት ይህ መድረክ፣ በዘንድሮው የሙዚቃ ዓመት ከተመዘገቡ አበይት ክንውኖች መካከል አንዱ ሆኖ አልፏል።

ኋይሉ በዚህ መድረክ ላይ

* ከተራራው ማዶ
* ዘመዳ ዘመዴ
* ማን እንዳንቺ
* ቆንጆ
* ይነጋል
* አዲስ አበባ የተሰኙ ዜማዎቹን የተጫወታቸው ሲሆኝ

እነዚህን የተመረጡ ሥራዎች ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በራሱ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለዕይታ በቅተው ከፌተኛ ተቀባይኘትን እያገኙ ይገኛሉ ። የሐይሉን ስራዎች ለመመልከት ሊንኩን በኮመንት መስጫው ላይ አስቀምጠነዋል ተመልከቱና ተዝናኑበት ።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: