የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
– በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
– ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
– አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
@tikvahethiopia
Source: Yeneta Tube









No comments yet.