የሀገር በቀል ሙዚቃ ንግስት ዶሊ ፓርተን
#Ethiopia | የዓለም አቀፍ የከንትሪ ሙዚቃ ንግስት፣ ድምፃዊትና የበርካታ በጎ አድራጎት ስራዎች ባለቤት የሆነችው ዶሊ ፓርተን በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
በስድስት አስርት ዓመታት የኪነ-ጥበብ ጉዞዋ ከ100 ሚሊዮን በላይ የሙዚቃ አልበሞችና ስራዎቿን በመሸጥ 11 የግራሚ አዋርዶችን ማሸነፍ ችላለች።
እንደ ጆሊን፣ አይ ዊል ኦልዌይስ ላቭ ዩ እና 9 ቱ 5 ያሉ ዓለም አቀፍ ተወዳጅነትን ያተረፉ ዜማዎችን በመጫወት ከ60 ዓመታት በላይ በሙዚቃው ዓለም ቆይታለች።
ከበርካታ ስኬታማ ሥራዎቿ መካከል በፈረንጆቹ 1973 ለአድማጭ የቀረበውና እስከ ዛሬ ድረስ በብዙዎች ዘንድ የማይረሳው ጆሊን የተሰኘው ዘፈኗ ይጠቀሳል።
ዶሊ ፓርተን እንደተናገረችው ይህ ዘፈን የተፃፈው ባለቤቷ ካርል ዴቪድ ዲን በባንክ ውስጥ በሚሠራበት ወቅት ከአንዲት ቆንጆ የባንክ ሰራተኛ ጋር ያሳየው የነበረውን ቀረቤታና ለእሱ ያደረገችውን ቅናት መሰረት በማድረግ ነው።
ጆሊን የሚለው ስም የመጣው ደግሞ በሙዚቃ ትርኢቷ ላይ ካገኘቻትና ፊርማዋን ከጠየቀቻት አንዲት ህፃን ልጅ ስም የተወሰደ ነው።
ዘፈኑ የተለመደውን የቁጣ ስሜት ሳይሆን አንዲት ማራኪና ውብ ሴት ፊት ተንበርክካ እባክሽን ባሌን አትውሰጂብኝ በማለት የምታቀርበውን የልመና ስሜት የሚያንፀባርቅ ነው።
የዘፈኑ መግቢያ የጊታር ምት እና የዶሊ ፈጣንና ስሜታዊ ድምፅ ዘፈኑ በሰዎች አእምሮ ውስጥ በቀላሉ እንዲቀረፅ አድርጎታል።
ስራው ከተለቀቀበት ጊዜ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አድናቂዎችን ያፈራ ሲሆን በሮሊንግ ስቶን የዓለማችን 500 ታላላቅ ዘፈኖች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።
ከማይሊ ሳይረስ እስከ በርካታ ዓለም አቀፍ ድምፃውያን ድረስ በራሳቸው የሙዚቃ ቅdirect መልሰው የተጫወቱት ዘመን ተሻጋሪ ስራ መሆን ችሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#countrymusic #usa #dollyparton #jolene #iwillalwaysloveyou #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.