ቴምር ፕሮፐርቲስ ለአካባቢ ጥበቃ ብርቱ ባለሙያዎች እውቅናና ሽልማት ሰጠ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በሪል እስቴት ዘርፍ ላለፉት 10 ዓመታት በላይ የዘለቀው ቴምር ፕሮፐርቲስ የንግድ ስራውን ከማህበራዊ ኃላፊነት ጋር በማጣመር ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የደን ጥበቃ ሬንጀሮች የእውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት አካሂዷል።

የጉለሌ እፅዋት ማዕከል እፅዋትን በመሰብሰብ፣ በማሰራጨትና ወደ ተፈጥሯዊ መኖሪያቸው እንዲመለሱ በሚደረጉ የምርምርና የጥበቃ ሥራዎች ወሳኝ ሚና ይወጣል። በማዕከሉ ሥር የሚገኙ ሬንጀሮችም የደን ሀብትን፣ ብዝሃ ሕይወትንና የሥነ-ምህዳርሚዛንን ለመጠበቅ በየዕለቱ ከፍተኛ ኃላፊነት ይወጣሉ፡፡

በመሆኑም ቴምር ፕሮፐርቲስ ወደ 75 ለሚጠጉ ሬንጀሮች ለሚያከናውኑት የማይተካ የደን ጥበቃ ሥራ ዕውቅና በመስጠት፣ ለሥራቸው ተስማሚ የሆነ ስጦታ አበርክቷል።በተጨማሪም “Plogging Ethiopia” በተባለው ተቋም አማካኝነት የወደቁ ፕላስቲኮችንና ቆሻሻዎችን በበጎ ፈቃደኝነት በመሰብሰብ ለአካባቢ ጥበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለአቶ ፍራኦል ክፍለወልድ ልዩ እውቅና ሰጥቷል።

​በሌላ በኩል ቴምፕ ፕሮፐርቲስ በመገናኛ በሚገነባው ዘመናዊ የሜጋ ፕሮጀክት ግንባታ ዙሪያ ከውጭ ሀገር የቻይና ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ከምድር በታች 8 ወለል (ቤዝመንት) እና ከምድር በላይ 18 ወለል የሚኖረውን የዚህን ህንፃ ግንባታ ለማፋጠንና የጥራት ደረጃውን ለመጠበቅ ከሁዋን አው እና ሳንሼንግ ከተባሉ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ተስማምቷል።

በዚህ ስምምነት መሠረት፣ Hui Chen የመሬት ቁፋሮ ሥራን ያከናውናል እንዲሁም Sansheng በበኩሉ የኮንክሪት አቅራቢ በመሆን በፕሮጀከቱ ይሳተፋል ተብሏል።

ድርጅቱ በዚሁ ተግባሩ የደንበኞቹን እምነት ያተረፈውን የሪል እስቴት ልማት ስራ ከማህበራዊና አካባቢ ጥበቃ ኃላፊነት ጋር አስተሳስሮ ለመቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል።

📸 ከበደ መክብብ

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: