በኔፓል በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ5መቶ በላይ ቢሻገርም ፤ በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረቶች ቀጥለዋል።

- Advertisement -
Sidebar AD

በኔፓል በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ5መቶ በላይ ቢሻገርም ፤ በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረቶች ቀጥለዋል።

ባለሥልጣናት እንደገለጹት በሂማላያ አዋሳኝ ክልል በደረሰው ቅጽበታዊ የጎርፍ አደጋ ምክንያት በኔፓል የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 5መቶ47 አድጓል።

አንድ የዕርዳታ ሠራተኛ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በኔፓል ያለው ሁኔታ ‹‹ሁከት የነገሠበት›› ቢሆንም አሁንም የጠፉ ሰዎች ‹‹በሕይወት ሊገኙ ይችላሉ››የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የኔፓል ባለሥልጣናት ከ1መቶ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎችን ማዳናቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣናቱ ቀደም ሲል ከ5መቶ በላይ ሰዎች መጥፋታቸውን ገልጸው ነበር።

በቲቤት ደግሞ 5 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ5መቶ58 በላይ የሚሆኑት መጥፋታቸውን የቻይና መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

እነዚህ አዳዲስ ቁጥሮች ቀደም ሲል ከተገለጹት ጋር የሚደመሩ ይሁኑ አይሁኑ ግልጽ አልተደረገም።

የአካባቢው ባለሥልጣናት ለቢቢሲ እንደገለጹት፤የተደረመሰው የበረዶ ግግር ከፍተኛ የጎርፍ ማዕበል ያስከተለ ሲሆን፤ማዕበሉም መኖሪያ ቤቶችንና መንገዶችን ያወደመ ከመሆኑም በላይ ዋናውን የኔፓል-ቲቤት የድንበር ማቋረጫ ዘግቷል።

ሀና ሰይፉ




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: