ቻይና አሜሪካ በኢራንና በንግድ አጋሮቿ ላይ ያወጣችውን አዲስ ማዕቀብ ‹‹ሕገ-ወጥ›› ስትል ተቃወመች

- Advertisement -
Sidebar AD

አሜሪካ በኢራን ላይ ያለውን የኢኮኖሚ ጫና ለማጠናከር አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ያላትን ዕቅድ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ፤ ቻይና እርምጃውን በጥብቅ ተቃውማለች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሜሪካ በኢራንና ከኢራን ጋር የንግድ ግንኙነት ባላቸው አገራት ላይ ለመጣል ያቀደችውን ማዕቀብ ‹‹ሕገ-ወጥ የአንድ ወገን ማዕቀብ›› ሲሉ ገልጸዋል።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት በበኩላቸው፤ከኢራን ጋር በገንዘብ የሚገናኝ ማንኛውም አገር፣ ባንክ ወይም ድርጅት ከአሜሪካ የማዕቀብ እርምጃ ሊያመልጥ እንደማይችል አስጠንቅቀዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ቻይና በኢራን የነዳጅ ገበያ ውስጥ ትልቁ ገዢ እንደሆነች ይገለጻል። ቤጂንግ ግን ከቴህራን ጋር ያላት የንግድ ትብብር በአለም አቀፍ ሕግ መሠረት እንደሚካሄድ በመግለጽ፣ አሜሪካ በግንኙነቱ ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደሌለባት አስጠንቅቃለች።

ይህ የቻይና ምላሽ የመጣው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር በሚቀጥለው ወር ውይይት ለማድረግ በሚጠበቁበት ወቅት ነው።

በተለይም ቻይና የዓለም አቀፍ ማዕድናትና ሌሎች ወሳኝ የማዕድናት ምርትና ማቀነባበር ውስጥ ትልቅ ድርሻ ስላላት በማዕቀቡ ምላሽ ቤጂንግ ተጨማሪ የንግድ እርምጃ ልትወስድ ትችላለች የሚል ስጋት በዋሽንግተን በኩል መኖሩ ተገልጿል።

በሌላ በኩል፤የኢራን ኢኮኖሚ ሚኒስትር አገራቸው ለአዲሱ የአሜሪካ ማዕቀብ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ኢራን የሁለት ዓመት ዕቅድ እንዳዘጋጀችና ከማዕቀቡ የሚመጡ ተጽዕኖዎችን ለመቆጣጠር የራሷ መንገዶች እንዳሏት ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ነው የዘገበዉ፡፡

ሰላማዊት ዲታ




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1