“እስከ 30 በመቶ የሚደርስ የበዓል የዋጋ ቅናሽ አድርጊያለሁ” –

- Advertisement -
Sidebar AD

ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ

#Ethiopia | ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የሚመጣውን የ2019 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኑረዲን መሐመድበቦሌ አትላስ እና በካዛንቺስ የሚገነቧቸውን አዳዲስ የመኖሪያ እና የንግድ ፕሮጀክቶች ለገበያ ማቅረባቸውን በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ስራ አስፈፃሚው በቦሌ አትላስ ሳይት የመሬት ደጋፊ ሥራ መጠናቀቁን እንዲሁም በካዛንቺስ 5 የቤዝመንት ደረጃዎች ተጠናቀው ህንፃው ግራውንድ ፍሎር ላይ መድረሱን አስረድተዋል።

እንደ አቶ ኑረዲን ገለፃ፤የመኖሪያ አፓርትመንቶች እና የንግድ ሱቆች ከ55 ካሬ ሜትር (Studio) እስከ 1መቶ65 ካሬ ሜትር (የሦስት መኝታ ክፍል) በካሬ ሜትር ከብር 80ሺ5መቶ ጀምሮ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ይህ ቅናሽ እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚቆይ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ድርጅቱ ደንበኞቹን ከዋጋ ንረት ለመጠበቅ የ‹‹ዋጋ ዋስትና››አሰራር መዘርጋቱን አስታውቋል።

በዚህም መሠረት በግንባታ ወቅት የውጭ ምንዛሬ ጭማሪም ሆነ የቁሳቁስ ዋጋ መወደድ ቢከሰት ደንበኞች በተዋዋሉበት የኢትዮጵያ ብር መጠን ብቻ ክፍያቸውን ፈጽመው በወቅቱ ቤታቸውን የሚረከቡ ይሆናል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: