የክብር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አህመድ ለታሪክ የተሰኘ የመጨረሻ አዲስ አልበሙን ለአድማጮች ሊያቀርብ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ለስድስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የማይተካ ሚና የተጫወተው የክብር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አህመድ፣ ለትውልድ የሚሻገር አዲስ የሙዚቃ አሻራ ለማስቀመጥ ያዘጋጀውን ለታሪክ የተሰኘ 26ኛ አልበሙን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

አልበሙ ለታሪክ የሚል ስያሜ የተሰጠው የቀደሙትን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቅርሶች፣ ውበትና ወግ ሳይለቁ ለአዲሱ ትውልድ ለማስረከብ ታስቦ ነው።

ሥራው የአርቲስቱን ልዩ የመድረክና የድምፅ ስልት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና ባህላዊ ቅኝቶች በተዋጣለት መልኩ ተዋህደውበታል።

በፍቅር፣ በሀገር፣ በህይወት ፍልስፍናና ማህበራዊ እሴቶች ላይ ያተኮሩ አዳዲስና በትዝታ የተቃኙ ዜማዎችንም አካትቷል።

በዚህ አልበም ዝግጅት ላይ አንጋፋና ወጣት የዜማና ግጥም ደራሲያን እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪዎች በጋራ ተሳትፈዋል።

አርቲስቱ አልበሙ የኪነ ጥበብ ህይወቱ የመጨረሻ ሥራ መሆኑን ገልጾ፣ አዲሱ የሙዚቃ ትውልድ የሀገርን ባህልና ቅኝት ሳይለቅ ዘመናዊነትን እንዲቀላቅል ጥሪ አቅርቧል።

አልበሙ በስፖቲፋይ፣ አፕል ሙዚክ፣ യൂቱብ እና በሌሎች ዲጂታል መድረኮች ለህዝብ የሚሰራጭ ሲሆን፣ በይፋ ከመልቀቁ በፊት በእንቁጣጣሽ ዋዜማ አንድ ነጠላ ዜማ፣ ሙሉ አልበሙ ደግሞ በመስከረም አጋማሽ ለአድማጮች ይደርሳል።

ይህንን ሥራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚያሰራጨው የሙዚቃ ኩባንያ ጋር በአጋርነት የሚያስተባብረው ይሳቃል ኢንተርቴይመንት ነው።

ይሳቃል ኢንተርቴይመንት የሀገራችን አንጋፋ ባለሙያዎች እንዲዘከሩ ከማድረግ ባለፈ፣ የሀገርን ባህልና ታሪክ በዓለም አቀፍ መድረኮች በማስተዋወቅና ደረጃቸውን የጠበቁ የሙዚቃ ድግሶችንና ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት ይታወቃል።

#mahmoudahmed #ethiopianmusic #letarik #yisakalentertainment #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2