የድሆችን መተዳደሪያ አናሳጣ፤ የተወሰነ ቦታ እንተውላቸው!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia| ቢል ጌትስ ድሆች የሚተዳደሩበትን እንኳን አናሳጣቸው ለእነሱ የሚሆኑ የተወሰኑ ቦታዎች እንተውላቸው ብለዋል።

የማይክሮሶፍት መስራቹ ቢል ጌትስ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በስራ ገበያው ላይ እያመጣ ያለውን ለውጥ ተከትሎ የተወሰኑ የስራ መደቦች ለሰዎች ብቻ እንዲተው ጥሪ አቅርበዋል።

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው ጌትስ ይህንን ሃሳብ ያቀረቡት AI በተለያዩ ዘርፎች የሰዎችን የስራ ድርሻ እየተረከበ ባለበት እና ወደፊትም ይህ አዝማሚያ እንደሚቀጥል በሚገመትበት ወቅት ነው።

ጌትስ AI ለሰው ልጅ ጠቃሚ ሊሆን ቢችልም ማህበረሰባዊ መረጋጋትን እና የሰዎችን መተዳደሪያ ለማረጋገጥ የተወሰኑ ስራዎችን ለሰዎች ብቻ ማቆየት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህ ሃሳብ እንዴት ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል ጌትስ በዝርዝር አላብራሩም።

ሆኖም ጥሪያቸው AI በስራ ገበያው ላይ እያመጣ ያለውን ተጽእኖ እና ወደፊት ሊኖሩ ስለሚገቡ እርምጃዎች የሚጠቁም ነው ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#America #Billgates
#AI #Human #work
#Economy #challenge


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2